Trendings

ቀጣናዊ ንግድን በጋራ ተጠቃሚነት የማሳደግ ራዕይን የያዘው የባሕር በር ጥያቄ

Spread the love

ለኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ከቀይ ባሕር ጋር የነበራት የንግድ ትስስር አሁን ላይ በአዲስ መልክ የስትራቴጂ፣ የብሔራዊ ጥቅም እና የደኅንነት ጉዳይ ሆኗል።

በፊዚክስ የኒውተን የመጀመሪያ የእንቅስቃሴ ሕግ እንደሚነግረን፣ አንድን ነገር ከቆመበት ለማንቀሳቀስ የመጀመሪያ ግፊት ያስፈልጋል። የሀገር እድገትም እንዲሁ በትናንት ቦታ ቆሞ የነገን ዓለም ማግኘት ስለማይቻል፣ አዲስ መዳረሻ ላይ ለመድረስ አዲስ እርምጃና እንቅስቃሴን ይጠይቃል።

የኢትዮጵያ የባሕር በር ራዕይ ከ30 ዓመታት በፊት በሴራ ያጣችውን የባሕር በር መልሶ ለማግኘት ብቻ የሚደረግ ጉዞ ሳይሆን፣ ዓለም አቀፍ ህግን መሰረት በማድረግ የአርሶ አደሩን እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ለማገናኘት፣ የሎጂስቲክስ ሥርዓትን ለማጠናከር እና የሀገር ውስጥ የእድገት ፍጥነትን እውን ለማድረግ የሚደረግ ጥረት ነው።

ይህ ጉዞ የሚሳካው በጉልበት ሳይሆን በውይይት፣ በዲፕሎማሲ እንዲሁም ሁሉም ተጠቃሚ በሚሆንበት የጋራ የልማት መንፈስ ነው። ቀጣናው በንግድ ሲገናኝ የሀገራት ኢኮኖሚዎች እርስ በርስ ይደጋገፋሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *