ክልሉ ያለዉን እምቅ አቅም ተጠቅሞ በዜጎች ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት:-የሱፐርቪዥን ቡድን::

Spread the love

የኢፌዲሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን ላለፉት 10 ቀናት በክልሉ ያካሄደውን ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ግብረ- መልስ ማጠቃለያ ውይይት በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ በክልሉ በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የተሰሩ የተገኙ ውጤቶች ለማስቀጠል ክህሎት መር ተቋማዊ ግንባታ በማጠናከር በየአካባቢ ተገንብተው ወደስራ ያልገቡ የማምራቸ እና መሸጫ ሼዶችን አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባት እንደሚጠበቅም ተናገረዋል።

በክልሉ ተናበው እና ተቀናቶ ለመስራት የተቋማት የጎንዮሽ እና የተዋረድ ግንኙነት በማጠናከር በትብብር መስራት አለበት ብለዋል።

የተጀመሩ የክህሎት መር ስልጠና ሰጪ ተቋማት ጥራት ደረጃ ዝቅተኛ መሆን፣ የብድር ስርጭትና አመላለስ ላይ ክፍተቶች እንዳሉ፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በክህሎትና ስልጠና የማሳደግ ተግባር አናሳ መሆኑን በግብረ-መልሱ ተመልክቷል፡፡

ተቋማዊ የውስጥ አደረጃጀት እና ተግባር ተኮር ስልጠና በመስጠት ለስራ ስምሪት ዝግጁ ለማድረግ ዜግችን ለስራ ስምሪት አብቅቶ መላክ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ክልሉ ለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ በመስጠት ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚሰራ ወሳኝ ተግባር በመሆኑ ድጋፉ ማጠናከር እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡

የግል ቴክንክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ዜጎችን የመቅረጽ ኃላፊነት ቢኖሯቸውም ተልዕኮአቸውን በብቃት ከመወጣት ውስንነቶች መኖሩን ና ይህንንም በአግባቡ መምራት እንደሚጠይቅ ገልጸዋል፡፡

በስራና ክህሎት ዘርፍ የሚታዩ የተሳሳተ አመለካከትን ለመቀየር በዜጎች አስተሳሰብ መቀየር ላይ ትኩረት ማድረግን የሚጠይቅ መሆኑን ሚኒስተር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ ገልፀዋል፡፡

ለስራ ዕድል ፈጠራ በተገቢው በማጠናከር እና ትኩረት በመስጠት በገንዘብ እና በመሬት አቅርቦት ማገዝ ይገባል ብለዋል፡፡

በክልሉ በቱሪዝም ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በቀጣይ ለስራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ አቅም መሆኑ በግብረ መልስ ሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡

የክልሉ መንግሥት ካለው ውስን በጀት ለስራ እድል ፈጠራ በመመደብ እያደረገ ያለው ስራ ውጤታማ መሆኑን ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ቡድን የገለፀ ሲሆን ቀጣይ ተጠናክሮ ማስካሄድ እንደሚገባም አንስተዋል ፡፡

ክልሉ ያለዉን እምቅ አቅም ተጠቅሞ ለዜጎች ስራ ዕድል ፈጠራ ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ በበኩላቸው በድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ግብረ- መልስ ያገኘናቸው መልካም አፈጻጸሞቻችንን በመጠቀም ፣ ክፍተቶችን ይበልጥ ለመሙላትና በቀጣይ ተግባሩን ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን ወደ ኢንተርፕራይዝ ማሻጋገሩ ጉዳይ በተገቢው ማጤንና የአሰራር ስርዓትን ተከትሎ ይሰራል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የፈዴራል ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ድጋፍና ሱፐርቪዥን በክልሉ እያደረገ ያለውን ድጋፍ ለቀጣይም አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቅሰው የክልሉ መንግሥት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ በልዩ ትኩረትና በቅንጅት የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ ተግባር እንዲጠናከር በየደረጃው ያለው የክልሉ አመራር በቁርጠኝት እንዲተጋም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።

የፈዴራል ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ቡድኑ ግብረ መልስ ለክልሉ ትልቅ አቅምና ተገቢ የሆነ በመሆኑ ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገልጸዋል፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *