


የሱፐርቪዥን ስራዉ በአፈጻጸሙ ሂደት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ለማጎልበት፣ድክመቶችን ለማረምና ለቀጣይ ስራዎች መሠረት እንደሚሆን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አቶ ፀጋዬ ማሞ ገለጹ።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ በተለያዩ ዞኖች፣ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ላይ የፖለቲካ ና የአደረጃጀት ስራዎች የህዋሳትና መሠረታዊ ድርጅት ያሉበት ደረጃ በመፈተሽ የመስክ ምልከታ ያካተተ ግምገማ አካሂዷል።
በመስክ ምልከታው ዝርዝር ሪፖርት ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል።
ምልከታ በተደረገበት መዋቅር ፣ የፓርቲ ተግባር በአሠራርና አደረጃጀት መመሪያን ተከትሎ በዕቅድ መመራቱ፣ አመራርና አባላት በተግባር ግንባር ቀደም መሆናቸው፣ የፓርቲ እሳቤን ማዕከል ተደርጎ በተሰጡ ስልጠናዎች ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸቸው በሪፖርቱ ቀርቧል።
ብልጽግና የበጎነት እሴት ልዩ መገለጫው በመሆኑ በሰው ተኮር ተግባር ዘረፈ-ብዙ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን
በህብረተሰብ ተሳትፎ አባላሉ ግንባር ቀደም መሆናቸውና በዘጠኝ ወራት በጥንካሬ የተመዘገቡ መሆናቸው በሪፖርቱ ተገልጿል።
አደረጃጀቶችን በተግባር አፈፃፀም ወደ ተሟላ ቁመና ከማምጣት ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ውስንነት፣ ሌብነትና ብልሹ አሠራር ላይ ወጥ የሆነ ትግል ከማድረግ አንፃር ከመዋቅር መዋቅር ያሉ ውስንነት መሻሻል እንዳለባቸው በጋራ መድረክ ላይ በአንክሮ የተነሱ ጉዳዮች ናቸው።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ማሞ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በፖለቲካ እና በአደረጃጀት ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉት የፓርቲው ስራዎች መሠረት ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
ጠንካራ አደረጃጀት መፍጠር የፓርቲው ቁልፍ ተግባር መሆኑን የገለጹት አቶ ፀጋዬ አደረጃጀቶችን በመፈተሽ ፓርቲው ባስቀመጠው አሰራር መሰረት ከአደረጃጀት እስከ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ በማጤን፣ የመደገፍና የማብቃት ስራን ተቋማዊ አድርጎ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ በቀጣይ ምልከታ ባልተዳሰሰበት አካባቢዎች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰዋል።
የፓርቲው የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ በበኩላቸው የፓርቲውን የአደረጃጀት ክፍተቶችን በመፈተሽ እንዲታረም ለማድረግ የተሰራው ስራ በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው ተናግረዋል፡፡
ከሱፐርቭዥ ምልከታ መነሻ ለቀጣይ ተግባሮቻችን እንደ መነሻ መውሰድ ይገባል ያሉት አቶ በላይ የታዩ መልካም ተሞክሮዎችን ለቅሞና ቀምሮ ማስፋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
በመጨረሻም በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከተቀመጠው ግብ አንፃር የተንጠባጠቡ ተግባራት ልዩ ዕቅድ ተዘጋጅቶ የርብርብ ማዕከል ለማድረግ የጋራ መግባባት በመፍጠር ወድረኩ መጠናቀቁን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ዘግቧል።
