ለማሻ ከተማ ሁለንተናዊ ዕድገት የድርሻቸውን እንደሚወጡ የማሻ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

Spread the love

በማሻ ከተማ በእጅጉ የተቀዛቀዘው የንግድ እንቅስቃሴ ችግሩ ለይቶ እልባት እንዲሰጠው ተጠይቋል።

በማሻ ከተማ አስተዳደር በመልካም አስተዳደርና አጠቃላይ የልማት ሥራዎች ዙሪያ በመድረኩ የተሳተፉት አካላት በከተማው እየተሰራ ያለው ልማት ለእኛ በመሆኑ የየድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።

የመድረኩ ተሳታፊ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት በከተማው በክልል በፌደራልና በአካባቢው መንግስት በርካታ የመሠረተ ልማት ስራ ተሰርተው የሚታይ ለውጥ በመኖሩ ይህን አጠናክሮ ማስቀጠል ከህዝቡ ይጠበቃል ብለዋል።

ማንኛውም ሰው ሰርተው ያገኘውን መልሰው በአካባቢው እንዲያፈስና የመንግስት አካልም ቀርቦ ህዝቡን በማወያየት የሚገባውን ገቢን በአሰራር መሠረት በመሰብስብና ለልማት ማዋል ያስፈልጋል ብለዋል።

ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ በከተማው የተጀመሩት የመሠረት ልማት ዝርጋታዎች ፍትአዊ እንድሆኑና በወቅቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንድውሉና ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችና ለልማት ተነሺ የሆኑ ሰዎችን የህብረተሰቡና የመንግስት ድጋፍ ታክሎበት ቅድሚያ ልመቻች ይገባል ብለዋል።

ማሻ ከተማ የከተማነትን ደረጃ ይዛ እንድትቀጥልና ለነዋሪዎች ምቹ ከማድረግ አንጻር ለአንድ ወገን የሚተው ጉዳይ አይደለም ያሉት ተሳታፊዎቹ እንደ ሀገር የተጀመረው የኮርደር ልማትና በፌዴራል መንግስት ከጎ-ማሻ-ቴፒ እየተሰራ ያለው መንገድ ስራን ህዝቡ ተባባሪ መሆን አለበት ሲሉ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

በአካባቢው በተለያዩ ልማቶች እየገቡ ያሉትን አልሚ ባለሀብቶች መንግስትም ሆነ የአካባቢው ህብረተሰብ ትኩረት ሰጥተው ልደግፍ ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።

በማሻ ከተማ ለተቀዛቀዘው ንግድ እንቅስቃሴ የጋራ አቅጣጫ ማስቀመጥ ያስፈልጋል ያሉት የንግዱ ማህበረሰብ ለየትኛውም ልማት ስራ ድጋፍ ከማድረግ ወደ ኃላ አንልም ሲሉ ተናግረዋል።

አንዳንድ ተጠሪነታቸው ለፌዴራል የሆኑ ተቋማት ማለትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማሻ ቅርንጫፍ ካለው ሰው ኃይልና አንጻር በአንድ መስኮት ብቻ ከፍተው ለደንበኞች የሚሰጡት ክብርና አገልግሎት ችግር ያለበት በመሆኑ ልፈተሹ ይገባል ብለዋል።

ከዚህ በፊት አካባቢው የሚዲያ ተደራሽነት የሌለውና አሁን ተቋቋሙ ስራ የጀመረው ማሻ ኤፍ ኤም የተለያዩ የልማት ስራዎችን በማጀብ ለአድማጭ ተመልካቾች እያደረሰ በመሆኑ ደስተኛ ነን ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ በተደራሽነት በኩል ትኩረት ተደርገው ቢሰራ የተሻለ ነው ብለዋል።

የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በበጎ ጎን ሲሆን ሀገር ይገነባል ከዚህ ወጪ ሀገርንም ሆነ አካባቢ ላይ ሌላ ችግር ስለሚፈጥር ተጠቃሚዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የመድረኩ ተናግረዋል።

የማሻ ከተማ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መልካሙ እንዳሻው ለውጡ መንግስት እንደ ሀገር ሰው ተኮር ስራን ትኩረት ሰጥተው እየሰራ የሚገኝ መሆኑን ተናግረው በዚሁ ለውጥ የተለያዩ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ከሆኑት አካባቢዎች ማሻ ከተማ አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

የማሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሠራዊት አየነው እንደገለጹት በከተማው የተጀመረውን መሠረተ ልማቶችን ከዳር ለማድረስ በጋራ መረባረብ አለብን ብለዋል።

ከተማው በብዙ መሠረተ ልማቶች ወደ ኃላ የቀረ ቢሆንም የለውጡ መንግስት በሰጠው ትኩረትና የህዝብ ድጋፍ ለውጦች እየታዩ ስለሆነ የመንግስት ተቋም አሰራርንና አገልግሎት አሰጣጥን በአሰራር ስርዓት እንደምፈትሹ የተናገሩት ከንቲባ አሁንም ቢሆን በሁሉም ዘርፍ የህዝቡ ድጋፍ በሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ እንገኛለን ሲሉ ተደምጠዋል።

በመድረኩ ሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶች የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ወጣቶች ሴቶች ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *