ብልጽግና ፓርቲ በሀሳብ ልዕልና እሳቤዎቹ ህዝብንና ሀገርን ለማሻገር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፦ አቶ ነጋ አበራ

Spread the love

ብልጽግና ፓርቲ በሀሳብ ልዕልና እሳቤዎቹ ህዝብንና ሀገርን ለማሻገር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ ገለጹ

የደቡብ ሞዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ “ትንተና ክህሎት ለአዳጊ መሪነት በሚል መሪ ሀሳብ ለፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ለመካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንደገለጹት ስልጠናው የአመራሩንና አባሉን አቅም በመገንባት እንዲሁም የበለጠ በማነሳሳት የብልጽግና ዕሳቤዎችን፣ ፕሮግራሞችን በአግባቡ በመረዳት ተልዕኮውን በሙላት መወጣት እንዲችሉ እና ያሉትን ክፍተቶችን ለመሙላት ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል።

ጠንካራ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችን በአቅም ግንባታ ስልጠና በመገንባትና የፓርቲውን ተልዕኮ በብቃት በመተግበር ብሎም የሁለንተናዊ ብልጽግና ጉዞን ለማፋጠን ዘርፉ ያለሰለሰ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አንስተዋል።

ብልጽግና ሀሳብ ማፍለቅ ብቻሞ ሳይሆን የፈለቀውን ሀሳብ በተደራጀ ሁኔታ መተግበር የሚችል ትልቅ ፓርቲ መሆኑን የገለጹት አቶ ነጋ በዚህም በአመራሩና በአባሉ ዘንድ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማጎልበት በርካታ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል።

በቀጣይ ከስልጠናው በሚገኘው ዕውቀት አመራሩና አባሉ የፓርቲው እሳቤዎችን በተገቢው በማስረጽ የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ሂደቶችን ማፋጠን እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደግፌ ኩድን በበኩላቸው ባለፉት የለውጥ ዓመታት በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፓለቲካው መስኮች ላይ አኩሪ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ጠቅሰዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ የሚገኝ ታላቅ ፓርቲ ነው።

በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅምግንባታ ዘርፍ ም/ኃላፊ አቶ ሙሳ አህመድ “ትንተና ክህሎት ለአዳጊ መሪነት በሚል መሪ ሀሳብ ለፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ለመካከለና አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጡ ይገኛል።

ስልጠናው ዛሬን ጠምሮ በተለያያ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስሆን በመድረኩ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *