




ክልላዊ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና በይፋ ተጀምሯል።
ዛሬ በይፋ በተጀመረው ክልል አቀፍ ምዘና በሁሉም ደረጃዎች ከ7200 በላይ ነባር መምህራን ፣ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀዉን የፅሑፍ ምዘና እንደሚወስዱ ታውቋል።
ምዘናውን በይፋ ያስጀመሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የሙያ ብቃት ምዘናው የመምህራንና የትምህርት አመራር እውቀትና ክህሎት ለማጎልበት እንደሚያስችል ተናግረዋል።
አቶ አልማው አክለውም በይፋ የተጀመረው የመምህራንና የትምህርት አመራር የሙያ ብቃት ምዘና በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች በ12 የተለያዩ ማዕከላት እና ወደ 24 በሚጠጉ የምዘና ጣቢያዎች እንደሚሰጥ አብራርተዋል።
የክልሉ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አካሉ አለማዬሁ በበኩላቸው ምዘናው እያንዳንዱ መምህራንና የትምህርት አመራር በሙያቸው ውጤታማ እንዲሆኑ በማስቻል ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል።
ምዘናውን በብቃት መወጣት ቀጣይ በሚኖረው የመምህራንና የትምህርት አመራር ጥቅማጥቅም ውጤታማነት ያለው ሚናም ከፍተኛ እንደሆነ ተብራርቷል።
የምዘናው የታርጫ ማዕከል አስተባባሪና የቢሮው የትምህርት ዕቅድ ዝግጅትና ሀብት ማፈላለግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አድማሱ ድብሎ በበኩላቸው ፈተናው ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም የባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን በተገቢው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በመጨረሻም የቢሮው ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ ለሁሉም ተፈታኞች መልካም እድል እንዲሆን መመኘታቸዉን የቢሮው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል ።
