
የዛሬው ቆይታ ከእኛ ጋር ፕሮግራማችን የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ በሚሰራቸው የስራ ዕድል ፈጠራ፣ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እና በአሰሪና ሠራተኛ ዘርፍ እየተከናወኑ ባሉ አጠቃላይ ተግባራት ዙሪያ ከቢሮ ኃላፊ ጋር ጋር ቆይታ አድርገዋል። መልካም ንባብ !
መ/ኮ፡- ስምና ኃላፊነትዎን ቢገልጹልኝ ?
ዶክተር አብይ፡, ዶ/ር አቢይ አንደሞ እባላለሁ፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ነኝ፡፡
መ/ኮ፡- በ2017 በጀት ዓመት እስከአሁን ያለው የስራ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል ቢገልጹልኝ ?
ዶክተር አብይ፦ የለውጡ መንግስት ብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚከተል በመሆኑ ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለማዕድን፣ ለቱሪዝምና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ሚዛናዊ ትኩረት በመስጠት እየተሠራ ያለ በመሆኑ ኢኮኖሚው በፍጥነት እያደገ ነው፡፡
የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ፖሊሲ በፈጠረው አመቺ አከባቢያዊ ሁኔታዎች በመታገዝ በአገራችን ባለፉት ተከታታይ ለውጥ አመታት ፈጣን ዕድገት ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን ለተመዘገበው ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት ሁሉም ዘርፎች ወሳኝ ሚና የተጫወቱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
መንግስት በሥራ ዕድል ፈጠራው ላይ በሰራው የሪፎርም ሥራ ውጤቶች እየተመዘገቡ ሲሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት በኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎት፣ በግብርና ዘርፉን ጨምሮ በርካታ ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉን የሚታወቅ ነው፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ መነሻ በማድረግ ባለፉት 10 ወራት ክህሎት መር የሆነ ስራ እድል ፈጠራ ስራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት በርካታ ውጤታማ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ፡፡
መ/ኮ፦ በስራ ዕድል ፈጠራ አኳያ በ2017 በጀት ዓመት እስከአሁን ምን ያህል የስራ ፈላጊ ዜጎች ልየታ ልዬታ ተከናዉኗል?
ዶ/ር አቢይ፡ በክልሉ ባለፉት 9 ወራት ፍላጎት ያላቸውን 126,490 ስራ ፈላጊ ዜጎችን በመለየት የስራ ስምሪት ለማመቻቸት በመሰራቱ እስካሁን ከነዚህ ወስጥ 35,794 ዜጎች በግብርና፣ በአገልግሎትና በኢንዱስትሪ ሥራ ዘርፎች ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጠሮላቸዋል፡፡
መ/ኮ፦ ቢሮው በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠ የሰጠ አጫጭር ስልጠና ካለ ቢገልጹ?
ዶ/ር አቢይ፡- እንደክልል በስራ ዕድል ፈጠራ የሚስተዋለውን የግንዛቤ ክፍተት ለመቅረፍ 23,503 ለሚሆኑ ለሥራ ፈላጊ ዜጎች፣ ለባድርሻ አካላት እና ለማህበረተሰቡ በንግድ ዕቅድ ዝግጅት፣ በአገልግሎትና በገበያ ትስስር በሥራ ዕድል ፈጠራ አሰራሮችና አማራጮች ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ዜጎች ሰርተው መለወጥ እንዲችሉና የቁጠባን ባህላቸውን እንዲያሳድጉ በተሰራው ስራ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተደራጅተው የሚሰማሩ ተጠቃሚዎች ቁጠባ ከ79,506,615 ሚሊዮን ብር ተቆጥቧል። በሁሉም ምርቶች የገበያ ትስሰር ድጋፍ በመፍጠር 218,412,998 ብር የገበያ ትስስር ድጋፍ በመስጠት 1508 ኢንተርፕራይዞች የድጋፉ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
መ/ኮ፦ የብድር አቅርቦት እና ሀብት ምደባ ተግባር አፈፃፀም ምን ይመስላል?
ዶ/ር አቢይ፡- ከሀብት ምደባ አንፃርም ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ መዋቅሮች ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚዉል ሀብት 37,740,000 ብር የተመደበ ሲሆን 8,823,000 ብር ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲውል ወደ ኦሞ ባንክ ተላልፏል፡፡
መ/ኮ፦ ኢንተርፕራይዞችን ውጤታማ ከማድረግ አኳያ ምን ተከናውኗል?
ዶ/ር አቢይ፡- ኢንተርፕራይዞች በተሰማሩባቸው የስራ ዘርፎች ውጤታማ እንዲሆኑ የብድር አገልግሎት እንዲመቻችላቸው ተደርጓል። ለአዳድስና ነባር ለ785 ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ 4,617 አንቀሳቃሾች ብር 80,360,168 ማሰራጨት ተችሏል፡፡ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተደራጅተዉ ወደ ሥራ ለገቡ ኢንተርፕራይዞች ከተሰራጨዉ ብድር ገንዘብ ከተዘዋዋሪ ፈንድ፣ ከውዝፍ ዕዳ እና ከዘመኑ ብድር 82,687,483 ብር ማስመለስ ተችሏል፡፡ ከተለየው የስራ ፍላጎት አንጻር በብድር ስርጭትና አመላለስ ዙሪያ ያለውን ማነቆ በፍጥነት በመፍታት ለበርካታ ዜጎች ወጤታማ የሥራ ዕድል ለመፍጠር በልዩ ትኩረት ይሠራል፡፡
በመካናይዘሽን እርሻ ለኢንተርፕራይዞች ለማስተላለፍ 2,411 ሄክታር መሬት የተለየ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 965 ሄክታር መሬት በ24 ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ 662 ተጠቃሚዎች በማስተላለፍ ወደ ስራ እንድገቡ ተደርጓል፡፡ ለዚህም 15 ትራክተሮችን የክልሉ መንግስት ገዝቶ ለዞኖች አሰራጭቷል፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ትራክተሮችን በአግባቡ ተጠቅሞ የሚጠበቀውን ውጤት ከማስመዝገብ አኳያ ሰፊ ክፍተቶች የሚታዩ በመሆኑ ትኩረት ሰጥቶ መሥራትን ይጠይቃል፡፡ እንደክልል ካለን ሰፊ የመሬት አቅምና የሥራ ፈላጊ ወጣቶች ቁጥር አንጻር አሁንም ሰፊ ሥራ የሚፈልግ በመሆኑ ሰፊ መሬት በማዘጋጀና አስፈላጊ ግብዓቶችን በማሟላት ወጣቶችን በስፋት ወደ ሥራ ለማሰማራት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅትና ትኩረት በመሥራት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው፡፡
ከዕድገት ደረጃ ሽግግር አኳያ በተለያዩ ዕድገት ደረጃዎች 252 ኢንተርፕራይዞችን ማሸጋገር የተቻለ ሲሆነረ 60 ሞደል ኢንተርፕራይዞችን መመልመልም ተችሏል፡፡ የተደራጁት ኢንተርፕራይዞች አዲሱን እሳቤን መሰረት አድረገው እንዲሰሩ በቅንጅት እየተሠራ ያለው ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
መ/ኮ፦ ለዜጎች የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት እንዲያገኙ ለማድረግ ምን ተሰርቷል?
ዶ/ር አቢይ፡- በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ከማመቻቸት አንጻር ከ3 ሺህ 700 በላይ ዜጎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፤ ነገር ግን ይህ ከዕቅድ አንጻር ዝቅተኛ በመሆኑ ቀጣይ ሰፊ ስራን የሚጠይቅ ተግባር ነው ።
መ/ኮ፦ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተደራሽነትና ለህብረተሰቡ ፍታሐዊነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት ብያብራሩልኝ?
ዶ/ር አቢይ፡- በመደበኛ መርሃ ግብር ወደ ቴክኒክና ሙያ የሚገቡ ነባር ሰልጣኞች 5856፣ አዲስ ሰልጣኞች 4480 እና በአጫጭር ስልጠና ወደ ቴክኒክና ሙያ የሚገቡ ሰልጣኞች ቁጥር 9078 ተችሏል፡፡ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሥልጠና እና የኢንተርፕርነርሸፕ ክህሎት ልማት አግባብነት፣ ጥራትና ተደራሽነት ማረጋገጥ የተቋማዊ አቅምና ብቃት ማሳደግ፤ አሰልጣኞችንን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር በሁለተኛ ዲግሪ ለማሰልጠን የኢንደስትሪ ውስጥ 1085 አሰልጣኞችን ማፍራት ተችሏል፡፡
ለህብረተሰቡ ችግር ፈች የሆኑ 27 የሩዝ መፈልፌያ ማሽን፣ የዶሮ መኖ ማቀበባበሪያ፣ የሻይ ቅጠል ማድርቅያ፣ የፍሳሽ ሳሙና ማምረቻ፣ የበቆሎ መፈልፈያ ቴክኖሎጂዎችን በማሸጋገር ህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል ፡፡ አሁንም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ከማፍራት በተጨማሪ የአካባቢውን ፀጋ መሰረት ያደረገ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል።
የክልሉ መንግስት ለዜጎች ሥራ ዕድል ፈጠራ የተሰጠው ትኩረት አበረታች ነው፤ በመሆኑም በሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ የሚታዩ ውስንነቶችን ጊዜ ሳይሰጡ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ በመፍታት ሥራ ፈጣሪ ዜጎችን ከክልሉ አቅሞች ጋር አጣምሮ ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
መ/ኮ፦ ለሰጡን ቃለ መጠይቅ መረጃ እናመሰግናለን
ዶክተር አብይ አንደሞ፦ እኔም አመሰግናለሁ!
