የኮሪደር ልማት ስራን የተረዱትና የተገበሩት ሞዴል አርሶ አደር አቶ አመነ አምበሎ!
በሸካ ዞን ማሻ ወረዳ የካንጋ ቀበሌ ሞዴል አርሶ-አደር አቶ አመነ አምበሎ ቤታቸውን እና ግቢያቸውን ውብ፣ ጽዱና ለመኖር ምቹ ማድረግ ከአባቶች የወረሱት ባህል ቢሆንም ፤ አሁን መንግስት በሰጠው ትኩረት ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። የቀለም ትምህርትን እስከ ሰባተኛ ክፍል እንደተማሩ የሚናገሩት ሞዴል አርሶ-አደሩ ፤ ስድስት ልጆችን በማስተማር ለውጤት ማብቃታቸውን ተናግረዋል። ባላቸው ዕውቀትና ትጋት ጽዱና ምቹ አካባቢን ከመፍጠር በላይ…
