


በኢትዮጵያ እስካሁን ከ15 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ አገልግሎት መመዝገባቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ኘሮግራም ገልጿል።
በዚህ ዓመት መጨረሻም ከ20 እስከ 23 ሚሊዮን ለሚሆኑ ነዋሪዎች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ የብሔራዊ መታወቂያ ኘሮግራም ምዝገባ ዳሬክተር አቶ ሄኖክ ጥላሁን ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ተናግረዋል።
አሁን ላይ 5 ሺህ የሚሆኑ የምዝገባ መሳሪያዎችን በመጠቀም አገልግሎቱ እየተሰጠ መሆኑን አቶ ሄኖክ ገልጸዋል።
በኢኮኖሚ ህብረተሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ፣ ወንጀልን ለመከላከልእንዲሁም ቀልጣፋ አገልግሎትን ለማግኘት የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወት ተመላክቷል።
በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ደግሞ 90 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎችን የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ ተጠቁሟል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
