በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቪ ተመሳሌታዊ አብነት የሚሆኑ ተግባራት በጉብኝቱ መመልከታቸዉን አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ

Spread the love

‎በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር ጨታ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር አቶ ተፈራ ሳካሎ ጅምር የአሳ ፖንድ ስራዎችን በሌሎች አርሶና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላይ ተሞክሮውን መቀመርና ማስፋት እንደሚገባ ተገልጿል።

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ከኮንታ ዞን አመራሮች ጋር ‎በአመያ ከተማ አስተዳደር ጨታ ቀበሌ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቪ አካል የሆነውን የአርሶ አደር ተፈራ ሳካሎ የአሳ ሀብት ልማት ሥራ ጉብኝት አድርገዋል።

‎በዚሁ ጊዜ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን እንደገለጹት በዕለቱ በአርሶ አደር ማሳ ላይ የተመለከቱት የአሳ ሀብት ልማት እንቅስቃሴ አበረታችና ተስፋ ሰጪ እንዲሁም ተሞክሮው ሊቀመር እንደሚገባ ገልጸዋል።

‎በየአካባቢው ያሉትን ፀጋዎች በመለየትና የፈጠራ እሳቤዎችን ተጠቅመው በቁርጠኝነት ከሰሩ ሀብት ማፍራትና የገቢ አቅምን ማሳደግ እንደሚቻል የዛሬው ጉብኝት አንዱ ማሳያ ነው።

‎አርሶ አደሩ በተቀናጀ የግብርና ልማት እያከናወነ ያለው ተግባር አጣናክሮ ለማስቀጠል የዘርፉ ባለሙያዎች እና አመራሮች ሁለንተናዊ ድጋፍን እንደሚያሻው ጠቅሰዋል።

‎የግብርና ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚችሉ አሰራሮችን አጠናክሮ በማስቀጠል የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥና ተረጂነትን ማስወገድ እንደሚገባ ጊዜው ይጠይቃል ብለዋል።

‎የአመያ ከተማ አስተዳደር ጨታ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር አቶ ተፈራ ሳካሎ በጉብኝቱ ላይ እንዳብራሩት አርሶ አደሩ ያለውን የእርሻ መሬት በአግባቡ አልምቶ ተጠቃሚ እንዲሆን ከመንግስት አመራሮችና ባለሙያዎች የሚሰጠው ትምህርት ውጤታማ እንድንሆን ያስችላል ብለዋል።

‎በተለያዩ የግብርና ስራዎች በሰብል ልማት ፣በቅመማ ቅመም ፣በእንስሳት እርባታ፣ በንብ ማነብ እና በአሳ እርባታ ዘርፎች ላይ ጠንክረው በመስራታቸው ጥሩ ገቢ እያገኙ መሆኑን በጉብኝቱ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *