ሪፖርታዥ

Spread the love

ሪፖርታዥ

ላለፉት 9 ወራት የአርብቶ አደሩን ኑሮ የሚያሻሽሉ ውጤታማ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን የአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ

በአርብቶ-አደር እና ከፊል አርብቶ አደር ማህበረሰብ አካባቢ ፈጣንና ፍትሐዊ ልማት ለማረጋገጥ  እንደ ሀገር የተነደፉ የፖሊሲ ማሻሻያዎችና ማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎችን ከክልላችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማስተሳሰር በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን ቢሮው ገልጸዋል፡፡

በአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ዘንድ የሚነሳውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በዕቅድ ለይቶ ከመፍታት አኳያ የነበረውን ውስንነት መቅረፍ በሚችል ሀገራዊ ፍኖተ ብልፅግና መነሻ ዓመታዊ ዕቅድ በማዘጋጀት በርካታ ተግባራት ተከናውኗል፡፡ 

በ2018 በጀት ዓመት ሊተገበሩ የሚችሉ የግንዛቤ ማሳደግ ስራ በትምህርት፣ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማት ሥራዎች፣የቆላማ አካባቢ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ተደራሽነት፣በአፈርና ውኃ አጠባበቅ እንዲሁም በአማራጭ የኑሮ ማሻሻያና ገበያ ትስስር መፈጠሩ ተገልጿል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በተመለከተ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በአርብቶ አደር ማህበረሰብ የአኗኗር ዘይቤ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ በመቀነስ ለልማትና መልካም አስተዳደር ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንዲቻል 33ሺህ 761 የህብረተሰብ ክፍሎችን ማወያየት የተቻለ ሲሆን አፈጻጸሙም 99.7% ላይ ይገኛል፡፡

ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ልየታ አንጻር በካፋ ዞን ጎባ ወረዳ እና በተቀሩት የምዕራብ ኦሞ ዞን ወረዳዎች በቀጣይ ሩብ ዓመታት የልየታና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በጥናት ላይ የተመሰረተ ስራ ለመስራት እንቅስቃሴ በቢሮ ደረጃ ተጀምሯል፡፡

የአርብቶና ከፊል አርብቶ አደር ልጆች በክልላችን በሚገኙ ሁለት ሆስቴሎች 172 ተማሪዎች የምግብ፣ የመኝታ፣ የትምህርት ቁሳቁሶችና ንጽሕና መጠበቂያ አገልግሎት እያገኙ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተደረገ ሲሆን በቢሮውና በዞን በጀት በአጠቃላይ በድፕሎማ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በ2ኛ ዲግሪ 110 የአርብቶ-አደርና ቆላማ አካባቢ ማህበረሰብ ልጆች የረጅም ጊዜ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ሆኗል፡፡

በእንሰሳት መሰረተ ልማት በ2017 በጀት ዓመት የተጀመሩ በካፋ ዞን የጎባ ወረዳ እና በምዕራብ ኦሞ ዞን የማጂ እንስሳት ጤና ኪሊኒክ ግንባታ በማጠናቀቅ አገልግሎት እንድሰጡ ማድረግ የተቻለ ሲሆን የጋቺት ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ የእንሰሳት ገበያ ማዕከል ግንባታ 95% ላይ ማድረስ ተችለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች 5 የእንስሳት ጤና ኪሊኒኮችና ግብይት ማዕከላት ግንባታ ፕሮጀክቶች ከ 85 በመቶ በላይ ማድረስ የተቻለ ሲሆን እስጀ በጀት ዓመቱ ማጠቃለያ በማጠናቀቅ 2ሺህ 800 ሴቶችን ጨምሮ 7ሺ 300 የአርብቶ-አደር ማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተጠቅሰዋል።

በካፋ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ባሉት የአርብቶ አደር አካባቢዎች 51 ሺህ 340 የእንስሳት ክትባት አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን 20ሺህ 402 የእንስሳት ህክምና አገልግሎት ለአርብቶ አደር ማህበረሰብ ክፍሉ መሰጠቱ ተጠቁመዋል።

በንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማስተባበር 16 አነስተኛ የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታዎች በሂደት ላይ ሲገኙ “በቆላማ የዜማ” ጥልቅ ጉድጓድ ውሃ ግንባታ መጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን “የባኒ” ጥልቅ ጉድጓድ ውሃና “ኪሉ” አነስተኛ መስኖ ግንባታዎች በቅርቡ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ ተመላክተዋል።

አርብቶ አደር ማህበረሰብን በመንገድ ለማስተሳሰር በካፋ ዞን ጎባ ወረዳ “ኡፊት-ጋራሙጂ 31 ኪ/ሜ መንገድ 60% ላይ ዩደረሰ ሲሆን ምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ “ቱልጊ-ካሪ-ሞጋ 20 ኪ/ሜ መንገድ 65% እንዲሁም ጎልዲያ ወረዳ”ጨበራ- ያርጦ” 30ኪ/ሜ የጠጠር መንገድ ግንባታ 60 በመቶ መድረሱ ተጠቁመዋል።

በቆላማ አካባቢ ኤክስቴንሽን የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በጠረጴዛ እርከን፣ በአፈር ካብ፣ በድንጋይ ክትርና ሌሎች ዘርፎች መሬትን ማልማት በመቻሉ አካባቢውን ለግብርና ስራዎች ምቹ በማድረጉ አርብቶ አደሩን ማህበረሰብ ወደ ወደዘርፉ የማስገባት ስራ ተጠናክሮ ቀጥለዋል።

የግብርና ኤክስቴንሽን ልማት ስራዎች ተጠናክሮ በመቀጠሉ 3ሺህ 750 የተሻሻሉ የእንቁላልና የስጋ ዶሮ ከነ ሙሉ ፓኬጅ ለ 150 ሞዴል ሴቶች በማቅረብ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ መቻሉ ተገልጸዋል።

አርብቶ አደሩን በግብርናው ዘርፍ በማሰማራት የምግብ ዋስትናቸውን ማስጠበቅ ላይ ትኩረት ተደርገው እየተሰራ ሲሆን 320 የተሻሻሉ የማር አመራረት ቀፎዎችን ከነ ሙሉ ግብዓቶች በማቅረብ 80 ወጣቶችን የስራ ዕድሉ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *