




በብልፅግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም በቴፒ ከተማ እየገመገመ ይገኛል።
የግምገማ መድረኩ ፓርቲው በ2018 በጀት ዓመት ያቀዳቸውን ግቦች በዘጠኝ ወራት ውስጥ ምን ያህል እንደፈጸመ በመፈተሽ፣ በቀሪዎቹ ወራት ለሚከናወኑ ተግባራት ግልጽ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የታለመ ነው።
በዚህም በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተከናወኑ ሥራዎችን በጥልቀት በመገምገም፣ የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን ለማጠናከር እና የታዩ ድክመቶችን በግልጽ ለይቶ ቀጣይ እርምጃዎችን ለመውሰድ ነው።
ይህም የፓርቲውን መደበኛ እና ኢንሼቲቭ አጀንዳዎች በተሻለ ቅንጅት፣ ተግባራዊነትና ውጤታማነት ለመፈጸም አቅም ይሆናል።
በመድረኩ ላይ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ፍቅሬ አማን ጨምሮ የክልል፣ የዞን፣ወረዳ እና የከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በፍቅር ከበደ
