ከጤና ዘርፍ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር የዉይይት መድረክ በሸካ ዞን እየተካሄደ ነዉ

“የጤናው ዘርፍ አርበኝነት ለሀገራዊ ዕድገት ” በሚል መሪ ቃል ከጤና ተቋማት ባለሙያዎች ጋር ዞን አቀፍ የውይይት መድረክ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ እንደገለፁት መንግስት በማህበራዊ ልማት ዘርፍ በተለይም የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን ለማሳደግ እንዲሁም አገልግሎቱን ለማዘመን በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በዚህም ተጨባጭ ለውጥ…

Read More

ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የዜጎችን ሁለንተናዊ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰቡ ክፍል የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ፦ አቶ ፍቅሬ አማን

‎ ‎በፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ሂደት የእስካሁኑ አፈጻጸም ፣ በተግዳሮቶች መፍትሔ መንገድና በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። ‎የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ “የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ያልተናነሰ ብሔራዊ ጥቅም…

Read More

በአካል የጠነከረ በኑሮ የበለጸገ አምራች ዜጋ ለሀገራችን እድገት ወሳኝ ሚና አለው ፦አቶ እንዳሻው ከበደ

በካፋ ዞን ከሁሉም መዋቅሮች የተወጣጡ ጤና ባለሙያዎችና አስተዳደር ሰራተኞች” የጤና ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር ዕድገት” በሚል መሪ ቃል ዞናዊ ውይይት እያደረጉ ነው። ሀገራችን የብዙ ጊዜ ታርክ ባለበት ከመሆኗ የተነሳ ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊና ማህበራዊ ለውጦችን በማምጣ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማስፋት የዚህ መድረክ ዋነኛ አላማ እንደሆነ የካፋ ዞን ዋና አሰተዳዳር አቶ እንዳሻው ከበደ ተናግረዋል። በአካል የጠነከረ እና በአዕምሮ የበለፀገ ትውልድን…

Read More

በክልሉ የትምህርት ምዘና እና የፈተና አስተዳደር ሥርዓትን ለማዘመን እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ ውጤቶች እየተመዘገቡ ናቸው- አቶ አልማው ዘዉዴ

”የዘመነ የፈተና አስተዳደር ሥርዓት ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም ሀገራዊና ክልላዊ የፈተና አስተዳደር የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። መድረኩን ያስጀመሩት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘዉዴ እንዳሉት፤ በትምህርት ሴክተር ሪፎርም ከተደረጉ ዋና ዋና ተግባራት መካከል የፈተና ምዘና እና የፈተና አስተዳደር ሥርዓት ማዘመን…

Read More

ፋይዳ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ እያንዳንዱ ህብረተሰብ መታወቂያውን በመያዝ መገልገል አለበት: አቶ በላይ ተሰማ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ ህዝቦች ክልል የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ (ፋይዳ) ማጠናከሪያ መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል። በማጠናከሪያ መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ ፓርቲው በለውጡ ካመጣቸው በርካታ ስትራቴጂዎች አንዱ ፋይዳ መታወቂያ ነው ብለው ይኸውም አንድ ሰው ራሱ ብቻ መሆኑን የሚያመለክት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ያለው መሆኑን ገልፀዋል። አቶ በላይ አክለው ይህ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በፓሪስ የሚገኘውን የኖትረዳም ካቴድራል ጎበኙ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ጉብኝቱ የቅርሱ መጠበቅን ባሕላዊ እና አለም አቀፍ ዋጋ ያመላከተ ነበር። እ.ኤ.አ በ2019 ከተከሰተው የእሳት አደጋ በኋላ የተደረጉ የጥበቃ ሥራዎች ፈረንሳይ ለታሪካዊ ምልክቶቿ ጠብቃ ለመጪ ትውልዶች ለማቆየት ያላትን ፅኑ አቋም የሚያሳዩ ናቸው ሲልም ገልጿል። ጉብኝቱ ለኢትዮጵያ ትርጉም ያለው ትምሕርት የሰጠ መሆኑን ጠቁሞ ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጎንደር ፋሲለደስ እስከ አባጅፋር…

Read More

የህብረተሰቡን የሰላምና የልማት ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ዙሪያ የመከረው ፎረም ቀጣይ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።

በፎረሙ ላይ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሁለቱ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና ተጋባዥ አካላት ተገኝተዋል። በመድረኩ በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ ተሳታፊዎች አስተያየታቸውን በመስጠት በህብረተሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶችን በመቅረፍ ለዘላቂ ሰላምና ልማት የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል ። በአንድ አካባቢ በህብረተሰቦች መካከል የሚፈጠረው ግጭት እየተባባሰ ሌላ የከፋ አደጋ እንዳያስከትል አመራሩ በሰከነ መንገድ…

Read More

የገጠር መሬት ይዞታ ማረጋገጥ በርካታ ፋይዳዎች ያሉት መሆኑን ባለሙያዎችና ባለይዞታዎች ገለፁ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ፣ በዘላቂ የመሬት አያያዝ ፕሮግራም (CALM) ድጋፍ ሁለተኛ ደረጃ የገጠር መሬት ምዝገባ፣ ማረጋገጥና የባለቤትነት ማረጋገጫ የካርታ ስርጭት ተግባር እየተከናወነ ይገኛል። አርሶአደር ገባነሽ ኬሮ እና አንጉቱ ኡራቾ በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ፣ የአንጊዮ ቆላ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆን፥ ማሳቸው የ2ኛ ደረጃ የገጠር መሬት ልኬት ተከናውኖ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መቀበላቸውን ይናገራሉ። የይዞታ ማረጋገጥ…

Read More

የ2018 በጀት ዓመት የካፒታል ፕሮጀክቶች የበጀት ዕቅድ እየተገመገመ ነዉ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የካፒታል ፕሮጀክቶች ዕቅድ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ኢንጂ.ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት እየተገመገመ ይገኛል። በግምገማ መድረኩ ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት ያለዉን ዉስን በጀት በካፒታል ፕሮጀክቶች ላይ በፍትሃዊነት፣በአዋጭነትና ከአስፈላጊነት አኳያ አይቶ በጀት መመደብ ያስፈልጋል ብለዋል። ከዚህ አኳያ ያለዉን ዉስን ሃብት አስቀድሞ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ለመጨረስ እንዲሁም ዉጤታማ ስራ ለመስራት የካፒታል…

Read More