



በፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ሂደት የእስካሁኑ አፈጻጸም ፣ በተግዳሮቶች መፍትሔ መንገድና በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ “የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ያልተናነሰ ብሔራዊ ጥቅም እንዳለው ገልጸውታል ሲሉ ተናግረዋል።
ፋይዳ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማፋጠን ከሃገራዊ ትልሞቻችን ጋር ተናባቢ ዕሳቤ እንዳለውና ይሄንንም ትልም ዕውን ለማድረግ ሀሉም ባለድርሻ አካላት በሙሉ አቅም መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ፋይዳ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ዕድገትና ለዘመነ አገልግሎት አሰጣጥ አስቻይ ከሆኑ መሰረቶች ውስጥ ዋነኛው መሆኑን የገለጹት አቶ ፍቅሬ በምዝገባ ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በፍጥነት በማረም የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት በቅንጅት መረባረብ ይገባል ተብለዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ እንደ ክልል የተያዘውን የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መተወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ ተግባራዊ ለማድረግ ከወዲሁ በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ያሉ ሲሆን በየአካባቢው የተሰሩ ስራዎችን በጥንካሬና በድክመት አብራርተዋል።
እስካሁን በተግባር አፈጻጸም ሂደት ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች በፍጥነት በማረም የተቀመጠውን ክልላዊ ግብ ለማሳካት በልዩ ትኩረት መከወን እንደሚገባ ጠቅዋል።
በመድረኩ የኢትዮ ቴሌኮም አመራሮች ፣የዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎች ፣የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶችና ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
