በአካል የጠነከረ በኑሮ የበለጸገ አምራች ዜጋ ለሀገራችን እድገት ወሳኝ ሚና አለው ፦አቶ እንዳሻው ከበደ

Spread the love

በካፋ ዞን ከሁሉም መዋቅሮች የተወጣጡ ጤና ባለሙያዎችና አስተዳደር ሰራተኞች” የጤና ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር ዕድገት” በሚል መሪ ቃል ዞናዊ ውይይት እያደረጉ ነው።

ሀገራችን የብዙ ጊዜ ታርክ ባለበት ከመሆኗ የተነሳ ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊና ማህበራዊ ለውጦችን በማምጣ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማስፋት የዚህ መድረክ ዋነኛ አላማ እንደሆነ የካፋ ዞን ዋና አሰተዳዳር አቶ እንዳሻው ከበደ ተናግረዋል።

በአካል የጠነከረ እና በአዕምሮ የበለፀገ ትውልድን ለመፍጠር የጤናን ተግባር በፊት ካለበት ከፍ ለማድረግ የጤና ተቋማትን የማስፋትና የመድኃኒት አቅርቦት እንዲጨምር በተቻለ መልኩ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የህዝባችንን አቅም መሠረት ያደረገ የጤና መድህን አገልግሎት ላይ ትኩረት ተሰጥተው መሰራት እንዳለበት ገልፀው አሁን አሁን እየጨመረ ያለውን የኑሮ ውድነትን በትንሹ ለመቀነስ የጤና ተቋማትን የልማት ቦታዎች የማድረግ ስራ መሰራት እንዳለበት ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል ።

በሀገራችን ውሰጥ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ለህዝባችን ግልፅ ማድረግና የማሳወቅ ሰራ መስራት የዚህ መድረክ ዋና አላማ መሆኑን የካፋ ዞን ጤና መምርያ ኃላፊ አቶ አክሊሉ አሰፋ አስረድተዋል።

በፊት የነበረው መከላከል መሠረት ያደረገ የጤና ፖሊሲ አሁን አክሞ ማዳን የተሻለ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረው ይህንም ለማጠናከር በአንድንድ አከባቢዎች የጤና ኤክስተነሽ ብቻ ያሉበት ቦታዎች ላይ ነርሶችንም በመመደብ ወጤታማ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንና ተግባሩም ተጠናክሮ እንደምቀጥል ገልፀዋል።

ለውይይት የተዘጋጀው ሰነድ በካፋ ዞን ጤና መምርያ ኃላፊ አቶ አክሊሉ አሰፋ የቀረበ ሲሆን በተሳታፊውች ሰፊ ውይይት እንደሚደረግም ይጠበቃል።

መድረኩ ላይ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ፣የካፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ንጉሴ፣ የካፋ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አክሊሉ አሰፋን ጨምሮ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተው ውይይቱን እየተሳተፉ ነው ሲል የዘገበው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *