ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በፓሪስ የሚገኘውን የኖትረዳም ካቴድራል ጎበኙ

Spread the love

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ጉብኝቱ የቅርሱ መጠበቅን ባሕላዊ እና አለም አቀፍ ዋጋ ያመላከተ ነበር።

እ.ኤ.አ በ2019 ከተከሰተው የእሳት አደጋ በኋላ የተደረጉ የጥበቃ ሥራዎች ፈረንሳይ ለታሪካዊ ምልክቶቿ ጠብቃ ለመጪ ትውልዶች ለማቆየት ያላትን ፅኑ አቋም የሚያሳዩ ናቸው ሲልም ገልጿል።

ጉብኝቱ ለኢትዮጵያ ትርጉም ያለው ትምሕርት የሰጠ መሆኑን ጠቁሞ ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጎንደር ፋሲለደስ እስከ አባጅፋር ጅማ ቤተመንግሥት እና በርካታ ቅርሶች ድረስ አቻ የማይገኝለት የታሪክ እና የባሕል ሀብት እንዳላት ሀገር ኢትዮጵያ ሀገራችን የቅርስ ጥበቃ እና እድሳትን ቅድሚያ የምትሰጥበት በርካታ ፀጋ አላትም ነው ያለው።

ቱሪዝምን ማስፋፋት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ቁልፍ የትኩረት መስክ በመሆን በኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ ከአምስቱ ምሰሶዎች አንዱ ሆኖ እየተሰራበት ይገኛል ሲልም ገልጿል።

ከአለም አቀፍ ምርጥ ተመክሮ በመማር ኢትዮጵያ የባሕል ሀብት ቅርሶቿን የመጠበቅ እና ቀጣይነት ያለው የቱሪዝም ልማት ሥራ ጥረቷን ለማጠናከር ትችላለችም ነው ያለው በመልዕክቱ ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *