Trendings

scs

Spread the love

ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ወራት ከሆርቲካልቸር ምርቶች ወጪ ንግድ ከ288 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስቴሩ ይህንን ያስታወቀው በዘርፉ የተሰማሩ ኩባንያዎች በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት የሰባት ወራት የሆርቲካልቸር ኢንቨስትመንት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ የምክክር መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ እንደገለጹት፤ የተጠቀሰው ገቢ የተገኘው ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት ከተላኩ የአበባ፣ የአትክልት እና የፍራፍሬ ምርቶች ነው።

እንደ ሀገር የግብርናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብና ሥርዓተ ምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባለፈ፣ ለወጪ ንግዱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ለማሳደግ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ጨምሮ ሌሎች የሪፎርም ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል።

በተለይም በቅርቡ የተደረገው የውጭ ምንዛሬ መመሪያ ማሻሻያ ለሆርቲካልቸር ዘርፉ ዕድገት የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል።

የዓመቱ የወጪ ንግድ ዕቅድ እንዲሳካ በየክልሎች ተጨባጭ ሁኔታ ያሉ ማነቆዎችን ለመቅረፍ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *