






















በዛሬው የደቡብ ምዕራብ ኢትጵያን ምን ያህል ያውቃሉ? በሚለው ፕሮግራማችን የካፋ ዞን የጤና ጥበቃ ሥራ ከየት ተነስቶ የት ደርሰ? የሚለውን አንቃኛለን፡፡
በካፋ ዞን የዘመናዊ የጤና ተቋማት እንቅስቃሴ ከባህላዊ ሕክምና ወደ ሚስዮናዊ አገልግሎት ከዚያ ወደ መንግስታዊ ጤና ተቋማት ወደ ጤና ኤክስቴንሽን ስርዓት በመሻሻል ዛሬ ምን ላይ ደርሶ ይሆን?
መልካም ንባብ!
ካፋ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ህዝቦች ክልል ውስጥ ከሚገኙ ስድሰቱ ዞኖች አንደኛው ሲሆን በ17 ወረዳዎችና በ378 ቀበሌዎች የተዋቀሬ ዞን ነው፡፡ የዞኑ ህዝብ ቁጥር በ2018 ዓ/ም 1,489,229 እንደሚሆን ከዞኑ ፕላንና ልማት መምርያ የተገኘ መረጃ የሚያመላክት ሲሆን የዞኑ ጠቅላላ ቆዳ ስፋት 10,602,7 ስኬወር ኪሎሜትር መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ዞኑ ከባህር ጠለላ በላይ ከ500-3500 ሜትር በባህር ጠለል በላይ ያለ ዞን ነው፡፡ የአየር ሁኔታን በተመለከተ ወይና ደጋ 70%፣ ደጋ 8%፣ ቆላ 22% መሆኑን ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡
በካፋ ዘመናዊ የጤና ተቋማት እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ አጠቃላይ የጤና ስርዓት ዕድገት ጋር ተያይዞ ደረጃ በደረጃ ተሻሽሎ መጥቷል። በ1950ዎች ውስጥ የክርስቲያን ሚስዮናዊያን የመጀመርያውን ዘመናዊ ህክምና ክልኒክ ከማደራጀታቸው አስቀድሞ የህክምና ስርዕቱ በካፋ ይታወቅ የነበረው ባህላዊ ሕክምና በአዋቂዎች ተመስርቶ ነበር።
ከባህላዊ ወደ ዘመናዊ የህከምና ስርዓት ለተደረገው ሽግግር ቦቦንጋ ከተማ በ1950ዎች የተገነባው ቦንጋ ክልኒክ እንደምሳሌ ተደርጎ ልወሰድ ይችላል፡፡
ይህ የሚስዮናዊን እንቅስቃሴ በካፋ በተለያዩ አከባቢዎች የዘመናዊ ህክምና እንዲስፋፋ መሰረት የጣለ ሲሆን በእነኝህ ሚስየናዊን አማካኝነት እስከ 1989 ዓ/ም ድረስ በአሁኑ ዴቻ ወረዳ በደቂያና በጭሪ (አውራዳ ከተማ አስተዳደር) አከባቢወች ክሊኒኮች ተገንብተው አገልግሎት ስሰጡ እንደነበር ከዞኑ ጤና መምርያ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ከምስዮኒያውን እንቅንቃሴ ባሻገር በ1950–1960 ዓ.ም አካባቢ የመጀመሪያ ዘመናዊ ክሊኒኮች እና ጤና ጣቢያዎች በመንግሰት ተገንብቶ አገልግሎት ስሰጡ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በካፋ ዞን ውስጥ የመጀመርያ የመንግሰት ጤና ተቋም ተደርጎ ልወሰድ የሚችለው የአሁኑ ቦንጋ ገብረጻድቅ ሻዎ ሆስፕታል ስሆን በ1961 ዓ/ም እንደ አንድ አነስተኛ ጤና ተቋም (ክሊኒክ) ተገንበቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይነገራል፡፡
ሆስፒታሉ መንግስት ባደረገው ልዩ ድጋፍ ከቦንጋ ጤና ጣቢያነት ወደ ዲስትሪክት ሆስፒታልነት ደረጃ ተሸጋግሮ አገልግሎት እየሰጠ ከቆየ በሁዋላ በተደረገዉ የመንግስት ድጋፍና ክትትል ግንባታዉ ተስፋፍቶ በ2005 ዓ.ም ወደ አጠቃላይ ሆስፒታልነት አድጎ የዞኑ ዋነኛ የህክምና ማዕከል ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡
ከ1989 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የተጀመረው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አሁን ላለው የጤና ስርዓት መሰረት የጣለ ዋነኛ ምክንት እንደሆነ ይነገርለታል፡፡በዝህም በዞኑ በእያንዳንዱ ቀበሌ የጤና ኬላዎች ተቋቋሙ።
መከላለከልን መሰረት ያደረገው ይህ የጤና ፖሊሰ በተለይ እናቶች እና ሕፃናት ጤና፣ ክትባት፣ የውሃ ንጽህና እና ንጽህና አገልግሎቶች ተሻሽለዋል። የእናት ሞት መጠን እና የሕፃናት ሞት በእጅጉ ቀንሷል። በካፋ ዞን ውስጥ የወረዳ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች እና ጤና ኬላዎች በስፋት አሉ።የተሻለ ላብራቶሪ፣ የምርመራ መሳሪያዎች እና የሕክምና ባለሙያዎች ቁጥር ጨምሯል።
ከዞኑ ፕላንና ልማት መምርያና ከዞ ጤና መምሪያ የተገኙ መረጃዎች አንድሚያመላክቱት በዞኑ በአሁን ሰዓት 299 መሰረታዊ የጤና ከላዎች፤ 3 አጠቃላይ ጤና ከላዎች፤ 50 ጤና ጣብዎች፤ 1 አጠቃላይና 5 የመጀመሪያ ደረጃ በጠቅላላው 6 ሆስፕታሎች፤ 1 የግል የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፕታልና 69 የግል መካከለኛ ክልንኮች በጥቅሉ 431 ጤና ተቋት ይገኛሉ ፡፡
በእነኝህ ጤና ተቋማት 54 ዶክተሮች፤ 151 የጤና መኮንኖች፤ 231 የድግሪ ምሩቅ ነርሶች፤ 31 ፋርማስት፤ 26 ላብራቶሪ ቴክኖሎጅስት፤ 14 ኮንፕርሄስፕ ሄልዝ ፕሮፌሽናል፤ 41 ሚዲዋይፍ ነርስ ፕሮፔሽናልና 93 ሌሎች ድግሪ እና ድፕሎማ ጤና ባለሙያዎች እንዲሁም 673 ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 2ሺህ በላይ የጤና በለሙያዎች አንደሚገኙበት መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በዞኑ የጤና ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ስሆን በ2018 በጀት ዓመት ከ164,187 በላይ አባወራና እማወራዎችን አባል በማድረግ ከ400 ሺህ በላይ ቤተሰቦችን የአገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል። ይህም ከተቀመጠው ግብ አንፃር 75% ማሳካት የተቻለ ስሆን ዓመታዊ መዋጮ መክፈል ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በየደረጃው ባለው መንግስት መዋቅር ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉንም ለማወቅ ተችሎዋል።
የጤና ተቋማት መስፋፋት፥የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያዎች (Health Posts) በአብዛኛው ቀበሌ ደረጃ መቋቋም፥ጤና ጣቢያዎች (Health Centers) እና ሆስፒታሎች ብዛት መጨመር ፥የእናትና ህፃናት አገልግሎት ክፍሎች ማሻሻል በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠውን የጤና ሽፋን ከማሳካት አንፃር በትክክለኛ መስመር እየተጓዘ ስለመሆኑ አመላካች ነው ማለት ይቻላል።
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች በትንሽ ክፍያ አገልግሎት እንዲያገኙ የተጀመረው የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ፥የጤና ወጪ በቀጥታ ከኪስ መክፈል (out-of-pocket expenditure) መቀነስ ፤መድሃኒት እና መሳሪያ አቅርቦት ማሻሻል
መሠረታዊ መድሃኒቶች በጤና ጣቢያዎች ማቅረብ፤ የላቦራቶሪ አገልግሎት ማሻሻልና በተለይ ሞዴል ፋርማስዎችን በሁሉም ጤና ተቋማት በማስፋፋት የመድሃኒት እጥረትና የዋጋ ጭማሪውን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት የጤና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የተያዘው ውጥን ስለመኖሩ ያመላክታል።
የተላላፊ እና ያልተላላፊ በሽታዎች እንቅስቃሴ ማላሪያ፣ ቲቢ፣ HIV እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ላይ ቁጥጥር፤ የደም ግፊት፣ ስኳር በሽታ እና ሌሎች NCDs ላይ ምርመራ መጀመር መከላከል ላይ ብቻ ተወስነው የቆየው የጤና ስርዓት አክሞ ማዳንንም ግብ አርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሎዋል።
በንጉሴ ወልደየስ
