“የላቀ የመከላከል አቅም ያለው የሰው ኃይል መገንባት ተችሏል” — ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ
የኢፌዴሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ፣ በጄትና በሄሊኮፕተር የበረራ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ አብራሪዎችንና የቴክኒክ ባለሙያዎችን በድምቀት አስመርቋል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፣ ተቋሙ ተለዋዋጭ የሆነውን የዘመኑን የጦርነት አውድ በሚገባ የተረዳና የላቀ የመከላከል ብቃት ያለው የሰው ኃይል መገንባት መቻሉን ገልጸዋል። በዕለቱ በጄት እና በሄሊኮፕተር በቂ…
