የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የ2018 በጀት ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ እያካኸደ ነው።

Spread the love

የምክክሩ መነሻ ነጥቦች ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ካሳ ውይይቱ በዋናነት ባለፉት 6 ወራት የተሰሩ ተግባራት አፈጻጸም ታይተው ለተቀሩት ተግባራት ጠቋሚ ነጥቦች ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ አክለው እንደ ገለጹት ባለፉት ጊዜያት ከክልል እስከ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ለተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ መሠረት ያደረጉ የግምገማ አፈጻጸም እንዲገለጹ ይደረጋል ብለዋል።

በወንጀል መከላከል ዘርፍ የመዝገቦች ምርመራ ኦዲት እንዲገለፅ አመላክተው ማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል አደረጃጀቶች ያሉበት ሁኔታ እንዲብራራ አመላክተዋል።

ህገ ወጥ ንግድ ለመከላከል እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ቢሆንም ህዝብ እንዲማረር የሚያደርጉት ነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር ላይ ጠንካራ ምልከታ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

ከትራፊክ ፍሰትና ቁጥጥር አገልግሎት ጋር በተያያዘ ጥልቅ ማብራሪያ እንደሚደረግ አሳውቀው እንደ ኮሚሽን በሁሉም ዞኖች በተደረገው ምልከታዎች የህብረተሰቡ መልካም አስተዳደር ችግር ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።

መንግስት ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት የሚያስተጓጉልና በፌክ አካወንት የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን አደብ ማስያዝ በሚያስችል መልኩ ለመስራት ሊዘጋጁ እንዲሚገባም አክለው ገልጸዋል።

ሀገሪቱ በተያዘው ዓመት የሚታካኺደው 7ኛ ምርጫ በክልላችን ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ከፖሊስ ተቋማት ሊደረግ የሚገባቸው ዝግጅቶች ላይ እንደሚመክሩም ተናግረዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የክልል ማዕከል፣ የሁሉም ዞኖች፣ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዦች እየተሳተፉ ሲሆን ዞኖች ለውይይት መነሻ የሚሆን የአፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛሉ።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *