ከተማን ከቀበሌ የሚያገናኘው መንገድ በመገንባቱ በአካባቢያቸው ይታይ የነበረውን የመንገድ ችግር እንደፈታላቸው በዳውሮ ዞን ኢሳራ ወረዳ ሾታ ቀበሌ ነዋሪዎች ተናገሩ።

Spread the love

በኢሳራ ‎ወረዳ የመንገድ ትስስር የምግብ ዋስትና ፕሮግራም (RCFSP) ከ2017 ዓም መጨረሻ ጀመሮ ከባሌ – መነሳ 16ኪሜ የመንገድ ጥገና፣1 የስትራክቼር እና ባሌ _ሾታ 12.37ኪሜ አዲስ የመንገድ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

በዳውሮ ዞን ኢሳራ ወረዳ ሾታ ቀበሌ አንዳንድ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት መንግስት የመንገድ ተደራሽነት ችግሮችን ለመቅረፍ በሰጠው ትኩረት ባሌ ከተማን ከሾታ ቀበሌ የሚያገናኘው መንገድ በመገንባቱ ከዚህን በፊት በአካባቢያቸው ይታይ የነበረውን የመንገድ ችግር እንደፈታላቸው ተናግረዋል።

ከዚህን በፊት መንገድ ባለመኖሩ አቅመ ደካማና እናቶች ለበርካታ ችግርና እንግልት ሲዳረጉ መቆየታቸውን በመግለፅ አሁን መንገድ መከፈቱ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች የሚቀርፍ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ምላሽ የሚሰጥ በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

የወረዳው የመንገድና ትራንስፓርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፋንታሁን ተካ እንደገለፁት፣የህብረተሰቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ብሎም የመንገድ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ክልሉ ከሌሎች አካላት ጋር በመተባበር እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

በተያዘው የበጀት አመት ከባለፈው አመት የዞረ በገጠር ትስስር ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም (RCFSP)‎ ከወረዳው ዋና ከተማ ባሌ-ሾታ የ12.37ኪ.ሜ አዲስ መንገድ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ እንዳለ በመጥቀስ ሌሎች የመንገድ ጥገና እና ስትራክቼር ስራዎችን በጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ሰለሞን ቀለመወርቅ እንዳብራራት፣በወረዳው ከ2017 በጀት ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ከ75 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ከተማን ከገጠር ቀበሌዎች ጋር ለሚያገናኘት በተጀመረው ተግባር ከባሌ – መንሳ የ16ኪሜ የመንገድ ጥገና፣አንድ የስትራክቼር እና 12.37ኪሜ አዲስ የመንገድ ግንባታ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በተጨማሪም በ2018 በጀት ዓመት ከዚህን በፊት ለህብረተሰቡ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት 15ኪ.ሜ አዲስ የመንገድ ግንባታ፣17ኪ.ሜ የመንገድ ጥገና፣2 የስትራክቼር እና የተንጠልጣይ ድልድይ ስራዎችን ለማከናወን በጨረታ ሂደት ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል።

ከተማን ከገጠር ቀበሌዎች ጋር ለማገናኘት እየተከናወነ የሚገኘው የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታ ስራው በጊዜ እና ጥራት እንዲጠናቀቅ አስፈለጊው የድጋፍ እና ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ የተናገሩት በክልሉ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ባለሙያ የሆኑት ኢንጂነር ምስጋና ናቸው ።

በካሳሁን አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *