


በኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል አለ የጤና ሚኒስቴር፡፡
የኢትዮጵያ ድንገተኛ የማሕበረሰብ ጤና አደጋ ፈጣን ምላሽና አመራር ስኬቶች እንዲሁም የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ቁጥጥር ማብሰሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ አጋር አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም ሚኒስቴሩ አክሞ ማዳን እና መከላከልን መሰረት በማድረግ የዜጎችን የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ለወረርሽኝ የማይበገር ጠንካራ የጤና ሥርዓት ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
በዚህ መሰረትም በቅርቡ በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉ ተገልጿል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
