
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የክልሉንና የዞኖች የ2018 በጀት አመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፃመ እየገመገመ ይገኛል፡፡
የግምገማ መድረኩን በንግግር የከፈቱ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ ምክር ቤቶች በሚያደርጉት የክትትትልና ቁጥጥር ስራዎች አስፈፃሚ ተቋማት በዕቅዳቸዉ መሠረት ተግባራትን በማከናወን የህብረተሰብ ተጠቃሚነት እንዲያሳድጉ በተከናወኑ ተግባራት ዉጤት እየተመዘገብ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ በህገ ማዉጣት፤ በጉባኤዎች አካሄድ፤ በህዝብ አስተያየት መድረኮች፤ በክትትልና ቁጥጥር ስራዎች፤ በአቅም ግንባታ ዘርፍ፤ በበጎ አገለግሎት፤ በሴቶች ኮኮስ አንዲሁም በኦዲት ግኝት አስመላሽ ግብረ ሃይል ዘርፍ በክልልና በየደረጃዉ በሚገኙ ምክር ቤቶች በ2018 በጀት አመት ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፃሞች ቀርበዉ አንደሚገመገሙ ዋና አፌ ጉባኤዉ ማብራራታቸዉን የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል፡፡
