



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ከምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ለከተማ አርቢዎችና ለባለሙያዎች የተዘጋጀ የክህሎት ማሻሻያ የአሰልጣኞች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።
በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክት ኃላፊና የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታመነ በቀለ የመድረኩ ዓላማ ለዘርፉ ባለሙያዎች የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠርና የከተማ ግብርና ራሱን ችሎ ባለመውጣቱ የተነሳ አፈጻጸሙን ለመገምገም አዳጋች በመሆኑ ይህን ችግር ከመፍታትም ባሻገር ዘርፉን ለማጠናከር ከሸያለመ እንደሆነ አንስተዋል።
አክለውም የከተማ ግብርና ለቴክኖሎጂ፣ መሠረተ ልማት እና ለገበያ የቀረበ በመሆኑ ከገጠር የተሻለ ምርት በማምረት ህብረተሰን ተጠቃሚ ማድረግ፣ የከተማ ግብርናውን ከሸማችነት ወደ አምራችነት ማሸጋገር እንደሚቻል በመጠቆም ምርቱን በሰፊው በማምረት ራስን ከመቻልም አልፎ ሌሎች የከተማ ነዎሪዎች መመገብና ገበያውን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እንዳለው አንስተዋል።
በመሆኑም በክልሉ የሚገኘውን ህዝብንም ሆነ የከተማውን ነዋሪዎች በጥቂት አልሚዎች ብቻ የምግብ ዋስትናውን ማረጋገጥ ስለማይቻል በከተሞች የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ተጨማር ሞዴል አልሚና አርቢዎችን ለመፍጠር የሚያግዝ ስልጠና በመሆኑ ሰልጣኞች በትኩረት እንዲሳተፉ አሳስበዋል።
ስልጠናው በሌማት ትሩፋት ፓኬጅ፣ በተሞክሮ ቅመራ ፓኬጅ፣ በአርቢዎች ተሞክሮ፣ በዶሮ እርባታ፣ በወተት ፓኬጅ፣ በመኖ ልማት አጠቃቀም፣ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት እንዲሁም የመስክ ጉብኝት ላይ ያተኮረ ሲሆን የስልጠናውን ሰነድ የክልሉ ከፍተኛ የዘርፉ ባለሙያዎች እያቀረቡ ይገኛሉ።
በስልጠናው መድረኩ ላይ የክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች፣ የዞን ግብርና ዘርፍ አመራር፣ የከተማ አስተዳደር የዘርፉ አመራና ባለሙያዎች፣ እንዲሁም ሞዴል አርቢዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በጌታሁን ግርማ
