


በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና መጠናቀቁን ፓርቲው አስታወቀ።
ከመስከረም 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የብልጽግና ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል።
በማጠቃለያ መድረኩም የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የስልጠናውን ማጠቃለያ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በሚመለከት የስራ ስምሪት ሰጥተዋል።
ስልጠናው ወሳኝ በሆኑ ሃገራዊ፣ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የፈጠረ ሲሆን ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ ሁለት ሺህ የፓርቲው አመራሮች ተሳትፈዋል።
የአቅም ግንባታ ስልጠናው በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች በቀጣይነት የሚሰጥ መሆኑን ከብልጽግና ፓርቲ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
