ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ ያነጋገርናቸው የሴቶች ገለፁ

Spread the love

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም የታርጫ ከተማ ሴቶች ተናግረዋል።

የአካባቢያቸውን ሰላም ከማስጠበቅ ባለፈ እድሜው ለመምረጥ የደረሰ የህብረተሰብ ክፍል ተመዝግቦ በምርጫ ድምጹን ለሚፈልገው ፓርቲ እንድሰጥ ለማስቻል የበኩላቸውን ድርሻ እንደምወጡ ወ/ሮ አለምቱ ባላ ገልጸዋል።

በሴቶች ተሳትፎ ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ እናሳካለን ያሉት ወ/ሮ አስናቀች ሳህሉ ሴቶች በምርጫው እንዲሳተፍ ከወዲሁ ተመዝግቦ ካርዱን በመያዝ የሚፈልጉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

ወ/ሮ አማረች ኡቴ የታርጫ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሁሉም ዜጋ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ በቀጣይ የሚያስተዳድረውን አካል መምረጥ እንዲችል የመራጭነት ካርድ አሁኑኑ ተመዝግቦ መያዝ እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የመራጭነት ካርድ ወስጅያለው ያሉት ወ/ሮ ዘነበች ዶኖቾ ሁሉም ሴቶች በህገመንግስቱ የተጎናፀፉትን ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በአግባቡ ለመጠቀም በየአካባቢያቸው በተመቻቹ የምርጫ ቦታዎች በመመዝገብ የመራጭነት ካርዳቸውን በጊዜው መውሰድ እንዳለባቸውም ገልጸዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *