7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ውጤታማ እንዲሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡ የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

Spread the love

የምርጫ ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የበኩላቸውን ድርሻ ከመወጣት በተጨማሪ የተሰጣቸውን የመምረጥ ዕድል በአግባቡ እንደሚጠቀሙም ያነጋገርናቸው የከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ለ7ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ የሚሳተፉት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊና ፍትሐዊ እንዲሆን ለማስቻል ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም የታርጫ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ በለጠ ባሹ ገልፀዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሃዊ ሰላማዊ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ሁላችንም ኃላፊነት መውሰድ አለብን ብለዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት መዘጋጀታቸውን የገለፁት ሌለኛው የታርጫ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ተረፈ ገብሬ ኢትዮጵያን በልማት ሊያሳድግና ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያደርስ ፓርቲን መምረጥ፤ ሰላሟን ለማፅናት የዜጎችም ድርሻ ልሆን ይገባል ገልጸዋል።

ዕድሜያቸው ለመምረጥ የደረሱት ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በነቂስ ወጥተው በአካባቢያቸው ወደ ሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ በመመዝገብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ አንድም ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ በሌላ በኩል ደግሞ የምርጫ ካርድ በመውሰድ የዜግነት ግዴታቸውን ሊወጡ እንደምገባም ያነጋገርናቸው የከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የወጣቶች ፌዴረሽን ፕረዚዳንት ወጣት በረከት ባሹ ምርጫው የሀገርን መጻዒ ዕጣ ፈንታ የሚወስን፥ ዜጎች ሕገመንግስታዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን የሚጠቀሙበት ጊዜ በመሆኑ ሁሉም ወጣቶች ይህን መብቱን በአግባቡ ሊጠቀሙ እንደሚገባም ነው የገለፁት።

በመጨረሻም 7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ዕድሜያቸው ለመምረጥ የደረሱት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሀገራቸውን ዕድል የሚወስኑበት በመሆኑ ምርጫ ቦርድ ባወጣ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ተመዝግቦ ካርድ በመውሰድ ለምርጫ ዝግጁ መሆን እንዳለበት ወጣት በረከት አስታውቋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *