በህገ-ወጥ ጦር መሳሪያ እና ኮንትሮባንድ ዝውውር የተጠረጠሩ 23 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ከጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት ሃያ ቀናት በስድስቱም ዞኖች ከሚገኙ የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ እና የክትትል ባለሙያዎች ባደረጉት ክትትል የተለያዩ ህገወጥ ቁሳቁሶችን እንዲያዝ አድርገዋል።

በዚሁ መሠረት የጦር መሳሪያዎች፤ቡና፤ኮሮሪማ፤ ናፍጣ፤ቤንዝል፤ሀሰተኛ ገንዘብ፤ለወንጀል መፈጸምና ወጣቶችን ወደ ወንጀል የሚገፋፋ የሺሻ ዕቃዎች እና ደን ውጤቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ 23 ተጠርጣሪ ግለሰቦች ከእነእግዚቨቱ እንዲያዙ የመረጃ እና ክትትል ስራ መስራቱን አመልክቷል፡፡

እንደ ኮሚሽኑ ወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ዳሬክቶሬት ገለፃ በክልሉ ሰው ህይወትና አካል ላይ ጉዳት የሚያደርሱ የጦር መሳሪዎች መካከል 6 ሽጉጥ ፤2 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፤1 ኃላቀር መሳሪያ፤200 የክላሽ ጥይቶች፤ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ ፀረ ሰላም ኃይሎች እጅ ሳይገባ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡

እንዲሁም በመንግስት ድጎማ በጀት ወደ ሀገር እንዲገባ የተደረገ ናፍጣ 18‚200 ሊትር፤ 5,000 ሊትር ቤንዝል፤460 ኪሎ ግራም ቅሽር ቡና፤121 ኩንታል ጀንፈል ቡና ፤ኮሮሪማ 40 ኩንታል፤87 ፍሬ ወይንም 17 ሺህ 400 መቶ ባለሁለት መቶ ሀሰተኛ ብር፤ 2‚195 የደን ውጤት ጣውላ እና 20 የሺሻ ማጨሻ ዕቃዎችን እንዲያዙ በማድረግ በ23 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ፖሊስ ምርመራ እያጣራባቸው መሆኑን በመረጃው አመልክቷል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ የህብረተሰቡ ሚና የጎላ መሆኑን ያመለከተው የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ የክልሉን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በሚደረግው እንቅስቃሴ ህዝቡ ከፀጥታ ጎን በመሆን መረጃ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪውን አቅርቧል ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *