መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎችን 100 ለማድረስ እየተሰራ ነው
በዚህ ዓመት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎችን 100 ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምክር ቤት አባላት አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ላነሱላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፥ በተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የነበረውን ቅሬታ ለመፍታት በርካታ ውጤታማ ስራዎች…
