“በሰላማዊ መንገድ ለሚመጣ ለመታረቅ አይደለም አብሮ ለማስራት ዝግጁ ነን “- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

በሠላማዊ መንገድ ለሚመጣ ማንኛውም አካል ለመታረቅ አይደለም አብሮ ለማስራት ዝግጁ ነን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ፤ በሰላማዊ መንገድ ለሚመጣ ለመታረቅ አይደለም አብሮ ለማስራት ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

መንግስት አሁንም በሰላማዊ መንግድ ለሚመጣ በሩ ክፍት መሆኑ ገልጸዋል።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ኢትዮጵያ ደካማ ሆና እንድትኖር የሚሹ ሀገራት ባሉበት ሁኔታ ብሔራዊ ጥቅምን አለማስቀደም ከፍተኛ ችግር ነው፡፡

ይሄ ችግር ባለበት ሰላም ማምጣት በራሱ ውጣ ውረድ አለው ያሉ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ብቻ እንደሚፈለግ አስረድተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፤ በሀገር ፍላጎት እስከተግባባን ድረስ የግሉን ጉዳይ ቸል ማለት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት የነበሩ ችግሮች ከስር መሰረታቸው ለማድረቅም የሽግግር ፍትህና ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ መሰራቱ ትልቅ እድል ነው ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *