Trendings

ኢትዮጵያ ለመገንጠልም፤ ለመጠቅለልም አትመችም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

Spread the love

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት አካሂዷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰላም እና በፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

‎ኢትዮጵያ ለመገንጠልም ለመጠቅለልም አትመችም፤ በሀገር ውስጥ የቆየው የእርስ በእርስ ግጭት መቆም አለበት የሚለው ሀሳብ ቅቡልነት እንዳለው ተናግረዋል።

‎

‎ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ደካማ ሆና እንድትኖርና በሁለት እግሯ እንዳትቆም የሚሹ እና የሚሰሩ አካላት ሰላም እንዳይሰፍን በእጅ አዙር እንደሚሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

‎

አንዳንዶችም የብሄራዊ ጥቅምን ካለመረዳት የተነሳ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ለጠላት ፍላጎትና ጥያቄ የተሰጡ አካላት መኖራቸውንም ተናግረዋል።

‎

‎ይህም በኢትዮጵያ የተሟላ ሰላም ለማምጣት እክል መሆኑን ነው ያመላከቱት።

‎

‎ኢትዮጵያን በጦርነት ማሸነፍ እንደማይችሉ የተረዱ አካላት፣ በተላላኪዎች አማካኝነት ለመረበሽ እንደሚሞክሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

‎

‎ይህ በዚህ እንዳለ መንግስት አሁንም ከታጠቁ ሀይሎች ጋር በሰላም ጉዳይ ላይ ለመወያየትና በጋራ ለመስራትም ዝግጁ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

‎

መንግስት ሰላም እንዲሰፍን ያለውን ቁርጠኝነት ከዚህ ቀደምም ከለውጡ ማግስት ማሳየቱን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ወደ ሰላም የተመለሱትና ልብ የገዙት ሰክነው ለአገራቸው እየሰሩ ሲሆን፣ መላላክ የለመደው ደግሞ ወደ እዚያው መመለሱን ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *