የፍትህ ሥርዓቱን የሚያሻሽሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

የፍትህ ሥርዓቱን የሚያሻሽሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት የፍትህ ሥርዓትን በሚመለከት ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ መንግሥት የፍትህ ሥርዓቱን ለማዘመንና ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የፍትህ ሥርዓቱ ነጻነትን እንዲጠብቅና የአሰራር ሥርዓቱን እንዲያሻሽል መንግሥት በቁርጠኝነት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በዘርፉ የሚስተዋለውን የአቅም ውስንነትን ለመቅረፍ የሙያተኞችን አቅም መገንባትና ቴክኖሎጂያዊ አሠራሮችን ማስረጽ ላይ የተጀመሩ ስራዎች የሚበረታቱ ናቸው ብለዋል።

በአጠቃላይ የፍትህ ሥርዓቱን ለማሻሻል በፍርድ ቤቶች የተጀመሩ የአሠራር ማሻሻያዎች በእጅጉ የሚበረታቱና ተጠናክረው የሚቀጥሉ ስለመሆናቸው በማብራሪያቸው ጠቅሰዋለ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *