October 2025
የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተጨባጭ ስኬት ያስመዘገበ መሆኑን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በ2017 ዓ.ም ኢትዮጵያ ታላላቂ የታሪክ እጥፋቶችን ያሳየችበት ስኬታማ እንደነበር በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ብዝኃ ዘርፍን መሠረት አድርጎ የተነደፈዉ ፖሊሲ ኢትዮጵያን ወደላቀ ብልጽግና እያሸጋገረ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣…
“አዲስ አበባ ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ አነስተኛ ስታዲየሞች ገንብተናል” ፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ አነስተኛ ስታዲየሞች መገንባታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ፤ አዲስ አበባ ውስጥ ከ1…
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጪ ንግድ ሸቀጦች ከአገልግሎት የበለጠ ውጤት አምጥተዋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጪ ንግድ ሸቀጦች ከአገልግሎት የበለጠ ውጤት አምጥተዋል አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት እየተካሄደ ባለው 6ኛ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ለምክር ቤቱ አባላት በሰጡት ማብራሪያ ነው። ባለፈው ዓመት ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም በአገልግሎት 8 ነጥብ 1 ቢሊየን…
በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፕሮጀክቶችን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ፡-
ፕሮጀክት በባህሪው እሳት ዳር እንደተቀመጠ ህፃን ነው፤ በየጊዜው ትኩረት እና ክትትል ይፈልጋል፣ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ ውስንነት አለ፣ ፕሮጀክቶችን እኔ የመንግስት ቅጥረኛ ነኝ፣ ኮንትራክተር ነኝ ከማለት ወጥቶ ቤቴን ነው የምሰራው ብሎ በማስብ ፕሮጀክቶችን አሳምሮ የመስራት ውስንነት አለ፣ መንግስት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የመጨረስ ችግር የለበትም፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የፕሮጀክት ፍላጎቶች እና የመንግስት የማስፈፀም አቅም ላይ ችግር…
በፌደራል መንግስት ብቻ 26ሺህ 500 ኪሎ ሜትር መንገድ እየተገነባ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
በፌደራል መንግስት ብቻ 26ሺህ 500 ኪሎ ሜትር መንገድ እየተገነባ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሮጀክቶች ክትትልን በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ 346 የመንገድ ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ…
በግብርናዉ ዘርፍ የተገኙ ዉጤቶች:-
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የግብርና ዘርፉ 7 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል፤ የግብርናው ዘርፍ በአጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ 2 ነጥብ 3 በመቶ ድርሻ አበርክቷል፤ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ የግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ እድገት አስመዝግቧል፤ በ2010 ዓ.ም የሩዝ ምርት 1 ነ ጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል የነበረ ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 63 ሚሊዮን ኩንታል ማድረስ ተችሏል፤ በስንዴ ምርት በለውጡ…
የኮሪደር ልማትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሰጡት ማብራሪያ
የኮሪደር ልማት የቦታና ጊዜ ምልከታን የሚቀይር ነው። ለአብነትም በአዲስ አበባ ብቻ ከአንድ ሺህ በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ተገንብቷል። በርካታ ወጣቶች ወደ ስፖርት እየተመለሱ ነው። ይህም ማህበረሰብን የመገንባት ስራ ነው። የትውልድ ስነ ልቦና ስብራትን እያረቀ ያለ ስራም ጭምር ነው። ይህን ማንም ሰው የሚያየው፤ ማንም ሰው የሚናገረው ጉዳይ ነው።
የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክትን በ24 ወራት ውስጥ አጠናቅቀን እንጨርሳለን
ልክ እንደተፈጥሮ ጋዝ ሁሉ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የድፍድፍ ነዳጅ ክምችት እንዳለ በሶስተኛ ወገን መረጋገጡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ነዳጅ ማጣሪያውንም በ24 ወራት ውስጥ አጠናቅቀን እንጨርሳለን ብለዋል። የጋዝና ነዳጅ ሥራ ከውጭ የሚገባውን ኃይል በመተካት የወጪ ምንዛሬ ለመቆጠብ ይረዳናል ሲሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለነዳጅና ለማዳበሪያ ከፍተኛ ሃብት ታወጣለች፤ ይህን ማስቀረት ከቻልን ብዙ ሃብት ለመቆጠብ ያስችላል ብለዋል። ከዚህ…
