በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፕሮጀክቶችን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ፡-

Spread the love

👉 ፕሮጀክት በባህሪው እሳት ዳር እንደተቀመጠ ህፃን ነው፤ በየጊዜው ትኩረት እና ክትትል ይፈልጋል፣

👉 የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ ውስንነት አለ፣ ፕሮጀክቶችን እኔ የመንግስት ቅጥረኛ ነኝ፣ ኮንትራክተር ነኝ ከማለት ወጥቶ ቤቴን ነው የምሰራው ብሎ በማስብ ፕሮጀክቶችን አሳምሮ የመስራት ውስንነት አለ፣

👉 መንግስት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የመጨረስ ችግር የለበትም፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የፕሮጀክት ፍላጎቶች እና የመንግስት የማስፈፀም አቅም ላይ ችግር አለ፣

👉 ኢትዮጵያ ውስጥ 346 የመንገድ ፕሮጀክቶች አሉ፣ 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ወጭ የሚጠይቅ ከ26 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ፕሮጀክት እየተሰራ ነው፣

👉 የመብራት ማመንጫ፣ ማስተላለፊያ እና ማከፋፈያ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ፣ በመብራት ብቻ የ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላርፕሮጄክት አለን፣ የ5 ቢሊየን ዩሮ ፕሮጄክት አለን፣ የ110 ቢሊየን ብር ፕሮጄክት አለን፡፡

👉 በተጨማሪም የፌዴራል መንግስት ከ200 ቢሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ አነስተኛ እና መካከለኛ ግድቦችን እየገነባ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *