



በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የግብርና ዘርፉ 7 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል፤
የግብርናው ዘርፍ በአጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ 2 ነጥብ 3 በመቶ ድርሻ አበርክቷል፤
በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ የግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ እድገት አስመዝግቧል፤
በ2010 ዓ.ም የሩዝ ምርት 1 ነ ጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል የነበረ ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 63 ሚሊዮን ኩንታል ማድረስ ተችሏል፤
በስንዴ ምርት በለውጡ ወቅት 47 ሚሊዮን ኩንታል ነበር፤
በየዓመቱ 1 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ስንዴ ከውጭ ይገባ ነበር፤
በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት 280 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማግኘት ተችሏል፤
በለውጡ ማግስት የቡና ምርት 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ነበረ
ከዘርፉ የተገኘው የውጭ ምንዛሬ 700 ሺህ ዶላር ነበር፤
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል የቡና ምርት ተገኝቷል፤
ከቡና ወጪ ንግድ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ማግኘት ተችሏል።
