ብዝሃ ዘርፍ ትብብርን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ የሰጡት ማብራሪያ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ በእጅጉ ውጤታማ ሆኗል። መንግስት ከህዝብ ጋር ተሳስሮ ልማት እንዲያመጣ ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠውም ከለውጡ ወዲህ ነው። ለአብነትም መንግስትና ህዝብ ተሳስረው በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት 48 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ችለዋል። ለዚህ ስኬት ደግሞ ከ25 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ሳይታክቱ በነጻ በየ ዓመቱ ወጥተው ችግኞችን መትከል ችለዋል። ይህም የመንግስትና ህዝብ…
