

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ መስጠት ጀምረዋል።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጡባቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ ዲፕሎማሲያዊ እና የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች አቅርበዋል።
በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
