ግብርናውን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተከናወነው ተግባራት ዉጤት እየተመዘገቡ ነዉ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ እየተገመገመ ይገኛል። የበጀት ዓመቱን የአፈጻጸም ሪፖርት የቀረቡት የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ፥ በክልሉ ግብርናውን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተከናወነው ተግባራት ውጤት እመመዝቡን በሪፖርታቸው አመላክተዋል። በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት፥ በመኸር የምርት ወቅት የተሻለ ምርት ለማግኘት ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ፣ በማሳ…
