




ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ክንፍ አደረጃጀት የተውጣጡ ወሰን ተሻጋሪ በጎ አድራጊ ልዑክ በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ አገልግሎት አከናውነዋል።
የልዑክ ቡድኑ አባላት በሆሳዕና ከተማ ለአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ የሚውል ቁሳቅስ፣ለህጻናት የትምህርት ቁሳቁስና የንጽህና መጠበቂያ አስረክበው የሌማት ቱሩፋት ልማትም ጎብኝተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ሽመልስ በስፍራው ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የበጎ ተግባር ህዝብ ለህዝብ ትስስርንና እህትማማችነትን ለማጠናከር እህቶች ረጅም ርቀት ተጉዘው ከሴቶች ክንፍ ተውጣጥተው የመጡ ልኡካንን በራሳቸውና በክልልሉ በብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስም አመስግነዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሰብለፀጋ አየለ በበኩላቸው ባለፉት ጊዜያት በሴቶች መሪነት በርካታ ስራዎችን በንቅናቄ ሲያከናውኑ መቆየታቸው በጎ ተግባርን ባህል እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።
የወሰን ተሻጋሪ ተግባር የእርስ በርስ ትስስርን በማጠናከር ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጎላ በጎ ተግባር ነው ብለው ለጋራ ልማትና ዕድገት በጋራ በመስራት የኢትዮጵያን ብለጽግና እውን ለማድረግ መረባረብ ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።ሴቶች በሰላም እሴት ግንባታ፣ በሀገር ልማት፣ በበጎ ተግባር በጎ ተጽዕኖ በመፍጠር ለቀጣይም አጠናክሮ እንዲቀጥሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በጎ የተደረገላቸው አካላት በዛሬው ዕለት ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል ሲል የዘገበው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ብልፅግና ፓርቲ ነው
በስፍራው የክልል፣የሀዲያ ዞን፣ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደርና ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አመራሮች፣ የሆሳዕና ከተማ የመንግስትና የፓርቲ የስራ ኃላፊዎችና አባላት ተገኝተዋል።
