




ጠንካራ የተደራጀ ክትትልና ድጋፍ ለላቀ ድልና ስከት በሚል መሪ ቃል የ2018 ዓ/ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የፓርቲ እና የመንግስት ሥራዎችን ለመስራት የክልሉ ድጋፍ ቡድን ከዳውሮ ዞን ፊት አመራሮች ጋር በቀጣይ ሥራዎችን ላይ የጋራ ውይይት አካሂዷል።
የአስተሳሰብ፣ የተግባርና የአሰራር ሂደትንና ውጤትን በመመዘን ክፍተቶች እንዲታረሙና መልካም ስራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ በምክትል ርዕሰ መሰተዳደር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ ገለጸዋል።
የድጋፋዊ ክትትልና ሱፐርቭዥን ስራዉ በጥብቅ ድስፒልን የሚመራ፣ ተግባራትን ወደፈፃሚዉና ታችኛዉ አደረጃጀት ድረስ ወርዶ በመመልከት፣ ጥንካሬና ጉድለትን በተጨባጭ መለየት ይገባል ብለዋል።
አቶ ፋጂዮ አመራሩ በአመለካከት የተግባር አንድነት በመፍጠር በዞኑ የተጀመረውን ጅምር ሥራዎችን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ወሳኝ በመሆኑ በየደረጃው ያለዉ አመራር በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበትም ገልጸዋል።
የፖለቲካና ስራዎች ከላይ እስከ ታች በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ተግባራትን በቁርጠኝነት በመፈጸምና በማስፈጸም ይገባል ያሉት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ባሻ የብልጽግና ቤተሰብና የብልጽግና ህብረት በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ትኩረት አድርጎ ውይይት ማድረግ እና ድሎችን በማስቀጠል መሻሻል ያለባቸውን ቶሎ የማረም ሥራ መሰራት ይገባል ብለዋል።
የህዝቡን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ በፓርቲያችን የተጀመሩት ኢኒሼቲቦችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል አስቻይ ሁኔታዎችን በመለየት የክልሉ ድጋፍ ቡድን ለተከታታይ 3 ወራት በዞኑ ዞንአቀፍ ሥራዎችን እንደምሰራም አስታውቋል።
በዞኑ ባሉት ወረዳዎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና በቀበሌዎች ደረጃ ቋሚ ባህል እስኪሆን ድረስ ተግባራትን አበክረን መደገፍና መስራት እንደሚገባ የክልሉ ፕላን እንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ ኃይሌ አስገንዝበዋል ።
ድጋፋዊ የሱፐርቪዥን ከስኬት ከመቀመርና ጉድለቶችን ከመማርና በተጨማሪ የተሻሉ አቅሞችን ወደ ታች ለማውረድ የሚያስችል መሆኑን ተገልጿል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
