
ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም (NIDP) በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ ዜጎች ወሳኝ ጥሪ አቀረበ! የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ (ጥቅምት 15 እና 16ን ቀን 2018 ዓ.ም.) ልዩ የፋይዳ መታወቂያ (Fayda ID) ምዝገባ ዘመቻ በከፍተኛ ንቅናቄ የሚካሄድ ይሆናል።
ይህ ዘመቻ መንግስት ለዜጎቹ ዲጂታል መታወቂያ እንዲኖራቸው የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ ሲሆን፣ መዝጋቢ አካላት በሙሉ በነዚህ ሁለት ቀናት የምዝገባ አገልግሎት ይሰጣሉ። በተለይም ብዙ ሰዎችን ማግኘት ወደሚቻልባቸው ስፍራዎች እንደ ትምህርት ቤቶችና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት ማዕከላት ተንቀሳቅሰው በመስራት የምዝገባ ሂደቱን ለዜጎች ተደራሽ ያደርጉታል።
በተለይም በስድስቱም ዞኖች ዋና ከተሞች የሚገኙ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።
ይህንን ወርቃማ ዕድል በመጠቀም ሁላችሁም ቅዳሜና እሁድ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት በመሄድ የፋይዳ መታወቂያ እንድትመዘገቡ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ጥሪውን ያቀርባል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ ህልም እውን የሚሆነው በሁሉም ዜጋ ተሳትፎ ነው!
