ግብርናውን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተከናወነው ተግባራት ዉጤት እየተመዘገቡ ነዉ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ እየተገመገመ ይገኛል።

የበጀት ዓመቱን የአፈጻጸም ሪፖርት የቀረቡት የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ፥ በክልሉ ግብርናውን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተከናወነው ተግባራት ውጤት እመመዝቡን በሪፖርታቸው አመላክተዋል።

በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት፥ በመኸር የምርት ወቅት የተሻለ ምርት ለማግኘት ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ፣ በማሳ ሽፋን እንዲሁም የግብርና ግብዓት አጠቃቀም የተሻለ እንደኾነም ገልጸዋል።

371ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ማሳ በመኸር ወቅት ዋና ዋና የአዝርዕት ሰብሎች መሸፈኑን የገለጹት ኃላፊዋ፣ የምርት ሂዴቱም ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ከአመታዊ ሰብሎች አፈጻጸም አኳያም የማሳ ሽፋንና የምርት ይዘት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ስነጻጸር የተሻለ አፈጻጸም ላይ እንዳለ ያነሱት ወ/ሮ ወሰነች፥ በቅመማ ቅመም እና የሻይ ልማትና ግብይት ላይም መሻሻል ተመዝግቧል ብለዋል።

የቡና ማሳ ሽፋን በማሳደግ ምርታማነትን ለማሻሻል የተሰጠው ትኩረት ውጤት እያስገኘ መኾኑን የጠቆሙት ወ/ሮ ወሰነች በዚሁም በሩብ ዓመቱ 4ሺህ 108 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን ገልጸዋል።

የግብርና ግብዓትና የገጠር ፋይናንስ አቅርቦት አፈጻጸም ከዕቅዱ አኳያ አመርቂ ውጤት መታየቱን የጠቀሱት ኃላፊዋ፥ በዚህም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ የዘር ብዜየት ስራዎች ተከናውኗል ብለዋል።

የኩታ ገጠምና ክላስተር እርሻ እንዲሁም መካናይዜሽን በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመኾኑ አፈጻጸሙን እየገመገሙ ማጠናከር እንደሚገባም ኃላፊዋ ተናግረዋል።

ያደረ የግብዓት ዕዳ አመላለስ ትኩረት የሚፈልግ መኾኑን ወ/ሮ ወሰነች አሳስበዋል ።

በእንስሳትና ዓሳ ሀብት የክልሉን አቅም በተሻለ መልኩ ጥቅም ላይ ለማዋል በመደበኛና በኢንሼቲቭ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ቢኾኑም በተላይ ጾታ ልይተው ማዳቀል ላይ ቀጣይ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *