
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ ክልሉ መሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ እንዳስታወቁት፣ በአንደኛው የሩብ ዓመት የመንገድ እና ድልድይ ጥገና ስራ ሲከናወን መቆየቱን ጠቅሰው በመንገድ ስራ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የዝግጅት ምዕራፍፎች ላይ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን አስታውቀዋል።
በተለይ ለማሽነሪዎች ጥገና ማድረግ ፣በሶስቱም ዲስትሪክቶች ነዳጅ ማስገባት እና ሌሎች ግብዓቶችን በተገቢዉ መልኩ ለማሟላት መቻሉን ገልጸዋል።
ስለሆነም ከዚህን በፊት ስንጠግን የነበረውን መንገዶች ከአሁን በኋላ በሙሉ አቅም ለመስራት የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን አስረድተዋል።
በአሁኑ ጊዜ በገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ኘሮግራም ከተጀመሩ ስድስት መንገዶች አራቱን ለማጠናቀቅ መቻሉን አውስተው ሁለቱንም ለማጠናቀቅ እርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
በተጨማሪም በሩብ ዓመቱ 79 ኪሜ አዳዲስ መንገዶች ለመጀመር ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ገልፀዋል።
በሩብ ዓመቱ የተሻሉ አፈጻጸሞችን በማጎልበት እና መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮችን በመለየት በቀሪ ወራት የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን ለማከናወን እንደሚተጉም አቶ ፋጂዮ ሳፒ ተናግረዋል።
በካሳሁን አሰፋ
