በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ጸጥታን ለማዝለቅ እና ለማጽናት ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በጋራ መስራት ወሳኝ ነው:- ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ
ሀገራዊና ክልላዊ ሠላምና ፀጥታን በአስተማኝ ደረጃ ለማረጋገጥ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል ውይይት በቦንጋ ከተማ ተደርጓል። በውይይቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እንደተናገሩት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በቅንጅት መስራት ሀገራዊና ክልላዊ ሰላምን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል። ክልላዊ የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ እንደተገመገመ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉ ከአጎራባች ሀገር ጋር የሚዋሰን በመሆኑ ከሀገር…
