በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ጸጥታን ለማዝለቅ እና ለማጽናት ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በጋራ መስራት ወሳኝ ነው:- ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ

Spread the love

ሀገራዊና ክልላዊ ሠላምና ፀጥታን በአስተማኝ ደረጃ ለማረጋገጥ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል ውይይት በቦንጋ ከተማ ተደርጓል።

በውይይቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እንደተናገሩት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በቅንጅት መስራት ሀገራዊና ክልላዊ ሰላምን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ክልላዊ የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ እንደተገመገመ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉ ከአጎራባች ሀገር ጋር የሚዋሰን በመሆኑ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር አብሮ በቅንጅት መስራቱ የሚገባ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሥራ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል አስራት ዶኖየሮ በበኩላቸው በክልሉ ባሉ አካባቢዎች የጸጥታ ስጋቶችን በመለየት በትብብርና በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል ውይይት መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በክልሉ በመንቀሳቀስ ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ለመስጠት ምክክሩ ወሳኝ እንደሆነም ሌተናል ጀነራል አስራት ገልጸዋል።

በክልሉ አስተማማኝ ሠላም ለማዝለቅ የተጀመረውን ስራ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምክክሩ ያግዛል ብለዋል።

ክልላዊ ሰላምን ለማጽናትና ለማዝለቅ ያለመ ወቅታዊ የዕቅድ ሰነድ በክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በአቶ አንድነት አሸናፊ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎች፣የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣የዞን አስተዳዳሪዎች ተሳትፈዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *