



የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡርን ትርፋማ ተቋም ማድረግ በሚያስችል የሶስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ።
ኢንጂነር ታከለ፥ ለሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ በተደረገው ውይይት የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡርን የውስጥ አቅም ለማጠናከርም ከመግባባት ተደርሷል ብለዋል።
በዚህም ተቋሙ ትርፋማ ለመሆን በሚያችለው የሶስት አመት ስትራቴጅክ እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን ‘በኤክስ’ ገጻቸው ጠቁመዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው ፥የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ጠንካራ እና ስራ ወዳድ ኢትዮጵያውያን እና ጅቡቲያዊያን የተሰባሰቡት ታሪካዊ ተቋም ነው ብለዋል።
በመሆኑም በሀሳብ፣ በሰው ሀይል እና ተቋም ግንባታ ላይ ለውጥ በማምጣት የሁለቱንም ሀገራት ተልእኮ ለመወጣት ከምን ግዜውም በላይ በትኩረት ለመስራትም መግባባት ላይ መደረሱን ነው የገለጹት ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
