በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ አፈጻጸም ተመዝግቧል፦ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የዩኒሰፍ ፕሮግራም አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ ገምግሟል። በክልሉ ዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ በስምንት ቢሮዎች እና በ17 ወረዳዎች የተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከናወነ ይገኛል። የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ በወቅቱ እንደገለጹት በ2016 በጀት ዓመት በክልሉ በዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ በስምንት ቢሮዎችና በ17 ወረዳዎች…

Read More

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል፡-

የምትሻገር ሀገር በማይሻገር ሐሳብ እየተናጠች ቆይታለች፣ የሚታረቅና የሚታረም የፖለቲካ ልዩነት እንደማይታረቅ ተደርጎ በመሠራቱ ሀገር በማይጠራ የፖለቲካ ሳንክ እንድትንገላታ ተገዳለች፣ የፖለቲካ ወለምታዎችን ለማቅናት ስብራቶችን ለመጠገን ስንጥቃቶችን ለመድፈን ስትል ዛሬም ለነገ የታሪክ የቤት ሥራ ለማስቀመጥ የሚደረጉት ሙከራዎች የሀገራችንን ፈተና አበርትተውታል፡፡ All reactions: 44

Read More

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአገራችን የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለውና ከህዝባችን ታሪክ፣ እሴቶች እና ማህበራዊ መስተጋብሮች ውስጥ የሚንጸባረቅና የተቆራኘ አገልግሎት እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል፡፡

በ1996 ዓ.ም ተቀርፆ ተግባራዊ የተደረገው የወጣቶች ብሄራዊ ፖሊሲ ክፍል አምስት ላይ ወጣቶች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የአካባቢ ጥበቃና ማህበራዊ አገልግሎት እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት ተሳትፈው እራሳቸውንና ማህበረሰባቸውን ሊጠቅሙ የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት እንደሚገባ በግልፅ ተቀምጧል፡፡ ይህንንም መሰረት በማድረግ በ2002 ዓ.ም የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በተቀናጀ አግባብ ለመምራትና ብዛት ያላቸው ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ እንዲሰማሩ ለማድረግ የሚያስችል…

Read More

በክልሉ የሚገኙ ፀጋዎችን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰርና በማስደገፍ ወደ ውጤት ለመቀየር እንደሚሰራ ተገለጸ።

የኢፌዴሪ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ኢኖቬሽን እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ባለድርሻ አካላት በሣይንስ እና ቴክኖሎጂ በአዲሱ ፖሊሲ ይዘት እና ስትራቴጂ አተገባበር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ቦንጋ ከተማ ሰጥቷል። የክልሉ ኢኖቬሽን እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛው ጋጊያብ በወቅቱ እንደገለጹት በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተዘጋጀው ፖሊሲ እና እስትራቴጂ በክልሉ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት…

Read More

የሸካ ጥብቅ ደን – የብዝሃ ህይወት ስብጥር ተምሳሌት

የሸካ ተፈጥሮ ደን ህብረተሰቡ በሀገር በቀል ዕውቀቱ በባህላዊ መንገድ ጠብቆ ያቆየው የማህበረሰቡ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እሴት ውጤት ነው። ደኑ እስከ አሁን የብዝሃ ህይወት ስብጥሩን ሳይለቅ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ መምጣቱ ህብረተሰቡ ለተፈጥሮ ሀብት ያለውን ተቆርቋሪነት የሚያመላክት ነው። ሸካዎች የተፈጥሮ ደኑ የምግብ፣ የመድኃኒት፣ የመጠለያና የመዝናኛ ምንጭ እና መሠረትም ነው ብለው ያምናሉ። በተለያዩ የተፈጥሮ ፀጋዎች የታደለው የሸካ ምድር…

Read More

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድን በበይነ መረብ (Digital system) ለመስጠት የሚያስችል ማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሄደ

በክልሉ ጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር እና የባለሙያዎች ፈቃድ አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልአዚዝ ፈረጃ እንደገለጹት የጤና ባለሙያዎች ከሚሠሩበት አካባቢዎች ሳይርቁ የሙያ ፈቃድን ዲጂታላይዝ ማድረግ መቻላቸው አላስፈላጊ እንግልት የሚያስቀር ነው። ከዚህ ቀደም ባለው የአሠራር ሥርዓት በአካል ወደ ክልል ጤና ቢሮ ድረስ በመገኘት በጊዜ፣ በገንዘብና በጉልበት መባከን ላይ ሲደርስ የነበረውን እንግልት እንደሚያስቀርላቸውም ተገልጿል። ከዚህ…

Read More