በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ አፈጻጸም ተመዝግቧል፦ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የዩኒሰፍ ፕሮግራም አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ ገምግሟል።

በክልሉ ዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ በስምንት ቢሮዎች እና በ17 ወረዳዎች የተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከናወነ ይገኛል።

የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ በወቅቱ እንደገለጹት በ2016 በጀት ዓመት በክልሉ በዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ በስምንት ቢሮዎችና በ17 ወረዳዎች በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ አፈጻጸም ተመዝግቧል።

በፕሮግራሙ ድጋፍ የክልሉ ውሃ ቢሮ በዳውሮ ዞን ዛባ ጋዞ ወረዳ ዴቺ ደነባ ቀበሌ የውሃ ግንባታ ስራ አጠናቅቆ በማስመረቅ ተጨባጭ ውጤት ማሳየቱን አብራርተዋል።

ከበጀት ስርጭትና አፈጻጸም አንጻር ዩኒሴፍ ፕሮግራም በበጀት ዓመቱ ለሴክተሮችና ወረዳዎች 59 ሚሊዮን 961 ሺህ 214.88 ብር የተሰራጨ ሲሆን ከዚህም 59 ሚሊዮን 192 ሺህ 234.92 በማወዳደቅ አፈጻጸሙ 98.72% በመሆኑን በመግለፅ በዚህም የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች መከናወናቸውንም አብራርተዋል።

የአፈጻጸም ጉድለት የታየባቸው በቀድሞ ክልል የተጀመረ የቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ቦይታ የውሃ ግንባታ፣በጤና ቢሮ በኩል የሚተገበሩ ሳኒቴሽንና ሀይጅን ትግበራ በወረዳዎች ላይ የታየው ዝቅተኛ አፈጻጸም ማሻሻል፣በጤና እና ትምህርት ቢሮዎች የበጀት አጠቃቀም እና አስተዳደር ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረምና ለማስተካከል በተያዘው ዓመት በቅንጅት እንደሚሰራም ኃላፊዋ ገልጸዋል።

በጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማጠናከር በተያዘው 2017 በጀት ዓመት የሚተገበሩ ተግባራትን ወቅቱን የሚመጥን ዕቅድ በማቀድ ካለፉት በተሻለ የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የቅንጅት ስራዎች እንደሚጠናከሩ የቢሮ ምክትልና የመንግስታት ትብብርና ሲቪክ ማህበራት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አለሙ ናቸው የገለጹት።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በክልሉ በዩኒሴፍ ገንዘብ ድጋፍ የሚተገበሩ ፕሮግራሞች የህዝቡ ሁሉዓቀፍ ተጠቃሚነት እንዲያረጋገጥ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ይበልጥ መጠናከር አለባቸው ብለዋል።

በመድረኩ በፕሮግራሙ የታቀፉ ሴክተሮች አፈጻጸም ረፖርት ቀረበው መሻሻልና መስተካከል የሚገባቸው ሀሳቦች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *