October 2024
በታርጫ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ክልል አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ምዘና ውድድር ተጠናቀቀ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ክልል አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ምዘና ውድድር ተጠናቀቀ፡፡ በውድድሩ የመዝጊያ ስነስርዓት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ ሃላፊ ተወካይና የስፖርት ተሳታፊነትና ውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በየነ ቴቃ ፕሮጀክቱ ለአራት ዓመታት ተቋርጦ በአዲስ ፎርማት…
ቡና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተጨባጭ ዋልታነቱን እያስመሰከረ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ቡና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተጨባጭ ዋልታነቱን እያስመሰከረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቡና ምርት ላይ ለተሰማሩ ውጤታማ አርሶ አደሮች፣ አልሚዎች፣ ቡና ላኪ ማኀበራት እና ባለሐብቶች ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥተዋል፡፡ ሀገራዊ የቡና ኤግዚቢሽን እና የዕውቅና መድረክ በሳይንስ ሙዝየም ተከናውኗል፡፡ በመድረኩ ላይ 64 የቡና ላኪዎች፣ አምራቾች እና የኢንቨስትመንት ተቋማት የዋንጫ እና የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡…
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እንደ ሀገር ከቡና ኤክሰፖርት ላደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እውቅና ተቸረው።
ክልልሉ እንደ ሀገር እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ አመት ለተገኘው 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከቱ ከኢፌዴሪ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እጅ የዋንጫ ተሸላሚ ሁኗል።
በቤንች ሸኮ ዞን የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ
በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ፤ ከበርታ ቀበሌ ልዩ ስፍራዉ ቆንጨልቃ መንደር ትናንት መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11 ጀምሮ በጣለዉ ከባድ ዝናብ አማካኝነት ትልቅ ዛፍ በመኖሪያ ቤት ላይ በመዉደቁ፤ አንዲት እናት ከወለደቻት ከሁለት ወር ሕፃን ልጇ ጋር ሕይወታቸዉ ማለፋን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ አስታውቋል። በተመሳሳይ በወረዳው ቂጤ ቀበሌ ልዩ ሥሙ ጋራ መንደር ተብሎ…
ኢትዮ-ግሪን ሞቢሊቲ 2024 ዓለም አቀፍ ዓውደ ርዕይና ሲምፖዚየም ቅድመ ሁነት ተካሄደ
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ኢትዮ- ግሪን ሞቢሊቲ 2024 በሚል ስያሜ በመጪዉ ህዳር ወር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ታላቅ ዓለም አቀፍ ዓውደ ርዕይና ሲምፖዚየም ያካሂዳል። የቅድመ ሁነት ፕሮግራሙ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የኢምባሲ ተወካዮች፣ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚሰሩ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የዘርፉ ባለሃብቶች እና ጥሪ ተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ትናንት መሰከረም 28/2017 ዓ.ም አመሻሽ…
2016 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣ ዓመት ነበር፦ የምጣኔ ሀብት ባለሞያ
2016 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቅ ለውጥ ያመጣ ዓመት ነበር ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሞያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ገለፁ። በበጀት ዓመቱ 8.16 በመቶ የነበረውን አጠቃላይ ሀገራዊ የምጣኔ ሀብት ዕድገት በቀጣይ ወደ 8.4 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱንም ባለሞያው በተለይ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል። በወጪ ንግድ ዘርፍም ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ጠቅሰዋል።…
ባለፉት 6 ዓመታት 11 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በኩታገጠም መልማቱ ተገለፀ
ባለፉት 6 ዓመታት 11 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በኩታገጠም መልማቱን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዝላታን ሚሊሲክ ጋር ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ ለዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ የግብርና ስራን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ግብርና የኢትዮጵያን አንድ ሶስተኛ አጠቃላይ እድገት፣ ሁለት ሶስተኛውን ኤክስፖርት እንዲሁም 65 በመቶ የገቢ ምንጭ እንደሚሸፍን አመልክተዋል። 25…
ኢትዮጵያ በተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ለ3ኛ ጊዜ አባል ሆና ተመረጠች
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ ከ2025-2027 በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሦስተኛ ጊዜ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች፡፡ ኢትዮጵያ ለሦስተኛ ዙር የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል በመሆን የተመረጠቸው በ79ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ነው፡፡ ቀደም ሲል በፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2015 እና ከ2016 እስከ 2018 ባለው ጊዜ ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ አባል በመሆን ማገልገሏ ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ ለሦስትኛ…
መንግሥት ከፍ ያለውን ድጎማ የሚያደርግበት ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ ተደረገ
መንግሥት ከፍ ያለውን ድጎማ የሚያደርግበት ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የነዳጅ ሪፎርም አፈጻጸም የደረሰበትን ደረጃ እና የቀጣይ አቅጣጫ አስመልክቶ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አማካሪ አህመድ ቱሳ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የነዳጅ የሪፎርም ሥራ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ጥሩ የሚባል ውጤት ማምጣቱን አንስተዋል። የሪፎርሙ…
