በቤንች ሸኮ ዞን የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

Spread the love

በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ፤ ከበርታ ቀበሌ ልዩ ስፍራዉ ቆንጨልቃ መንደር ትናንት መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11 ጀምሮ በጣለዉ ከባድ ዝናብ አማካኝነት ትልቅ ዛፍ በመኖሪያ ቤት ላይ በመዉደቁ፤ አንዲት እናት ከወለደቻት ከሁለት ወር ሕፃን ልጇ ጋር ሕይወታቸዉ ማለፋን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ አስታውቋል።

በተመሳሳይ በወረዳው ቂጤ ቀበሌ ልዩ ሥሙ ጋራ መንደር ተብሎ በሚጠራ ሥፍራ ከቀኑ 11:30 ሰዓት አካባቢ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለዉ ከባድ ዝናብ ምክንያት ዝናቡን ለመጠለል ዛፍ ሥር የነበረች አንዲት ግለሰብ ዛፋ ወድቆባት ሕይወቷ ማለፏን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር አዳነ አለማየሁ ተናግረዋል።

በአደጋዉ ቡና ለመልቀም የተሰማሩ ሠራተኞች በተሰራላቸዉ ዳስ ዉስጥ እያሉ ዛፍ ወድቆባቸዉ በአንድ ሰዉ ላይ ከባድ ጉዳት እና በሰባት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ ወደ ሕክምና ተወስደዉ ሕክምና እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

“ሕብረተሰቡ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ዛፍ ስር ከመጠለል እንዲቆጠብና አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ዛፎችን ከመኖሪያ ቤቶች አካባቢ በመቁረጥ መሰል አደጋዎችን መከላከል ይኖርበታል” ሲሉ ኢንስፔክተር አዳነ መልዕክታቸዉን ማስተላለፋቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት መረጃ ያመላክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *